
ባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤውን የፊታችን የካቲት 26 እንደሚያካሂድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በየካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚያካሂድ በመግለጽ የቦርዱ ታዛቢዎች እንዲገኙ ጠይቋል፡፡ ጉባኤውን የሚታዘቡም ወ/ሮ ቀነኒ እንሰርሙ እና ወ/ሮ በላይነሽ አላምረው እንዲሁም ጠቅላላ ጉባኤው በምስልና ድምጽ የሚቀርጹ ወ/ት ሮዛ አምሳሉ መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል።
Source: Link to the Post