You are currently viewing #ባሕርዳር‼️ ***** በጣና ሀይቅ በስተደቡብ ዳርቻ ላይ የምትገኘው ባህርዳር ከኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከአዲስ አበባ ከተማ በ565 ኪሎሜትር  ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታ…

#ባሕርዳር‼️ ***** በጣና ሀይቅ በስተደቡብ ዳርቻ ላይ የምትገኘው ባህርዳር ከኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከአዲስ አበባ ከተማ በ565 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታ…

#ባሕርዳር‼️ ***** በጣና ሀይቅ በስተደቡብ ዳርቻ ላይ የምትገኘው ባህርዳር ከኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከአዲስ አበባ ከተማ በ565 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምሥራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ ባሕርዳር በታላቁ ጣና ሀይቅና በአባይ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ፣ ለእንግዶችና ለጎብኝወች እጅግ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀይማኖታዊ ታሪካዊ የተፈጥሮና ሰውሰራሽ የቱሪስት መዳረሻ ቦታወች፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ሪዞርቶችና ሎጅዎች መገኛ እንዲሁም እንግዳ ተቀባይ የሆነ ህዝብ መኖሪያ በመሆኗ የኢትዮጵያ ሪቪዬራ በመባል ትታወቃለች፡፡ 👉የባሕርዳር የተፈጥሮ ስጦታ ጣና ሀይቅ፦ የጣና ሀይቅ በኢትዮጵያ ትልቁ ነው። ሀይቁ ሀይቅ ብቻ ሳይሆን አባይ ወንዝ መነሻ የሆነ አስደናቂ የተፈጥሮ ስጦታ ነው ። የከተማዋና የጣና ሀይቅ ዳርቻወች ልምላሜ፣ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው የአእዋፍ ዝማሬዎች እና በጣና ሐይቅ ውስጥ የሚገማሸሩ ጎማሬዎችና የተለያዩ እንስሳት ትእይንት እይታዎች ማራኪ ናቸው። ጣና በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ከሰኔ 1 ቀን እስከ ሰኔ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉባኤውን ያካሄደውና የብዝኃ ሕይወት ጉዳይን የሚመረምረው ዓለም አቀፉ ምክር ቤት ጣና ሐይቅን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኒስኮ በያዘው ብዝኃ ህይወት ክምችት በቅርስነት መዝግቦታል። ጣና በአጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩት 27 ገዳማትን አቅፎ ይዟል።ገዳማቶች በ14ኛ ምእት ዓመት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ባመነኮሷቸው ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ተብለው በሚጠሩት ቅዱሳን አባቶች የተመሠረቱ ናቸው። 👉ከገዳማቶች መካከል፦ ✔️ደብረ ማርያም፣ ✔️ክብራን ገብርኤል፣ ✔️ዑራ ኪዳነምህረት፣ ✔️መሀል ዘጌ ጊዮርጊስ፣ ✔️አቡነ በትረ ማርያም፣ ✔️አዝዋ ማርያም፣ ✔️ዳጋ ኢስጢፋኖስ፣ ✔️ይጋንዳ ተለሃይማኖት፣ ✔️ናርጋ ስላሴ፣ ✔️ደብረ ሲና ማርያም፣ ✔️ማንድባ መድኃኒዓለም፣ ✔️ጣና ቂርቆስ፣ ✔️ክርስቶስ ሳምራ ገዳም፣ ✔️ራማ መድሕኒ ዓለም፣ ✔️ኮታ ማርያም…እና ሌሎችም ገዳማቶች ይገኙበታል። 👉ሰባቱ ከዋክብት የሚባሉት፦ ❶ አቡነ ታዴዎስ~ደብረ ማርያም መሥራች ❷ አቡነ ዘዮሐንስ~የክብራን እና የእንጦስ ገዳም መሥራች ❸ አቡነ በትረማርያም~የዘጌ ጊዮርጊስ መሥራች ➍ አቡነ ኂሩተ አምላክ~የዳጋ እስጢፋኖስ መሥራች ➎ አቡነ ኢሳይ~የመንዳባ መድኃኔዓለም መሥራች ❻ አቡነ ዘካርያስ~ደብረ ገሊላ መሥራች ❼ አቡነ ፍቁረዮሐንስ~ጣና ቂርቆስ መሥራች ናቸው። 👉ጣና ቂርቆስ፦ ጣና ቂርቆስ ታቦተ ጽዮን ለ800 ዓመታት ያረፈችበት፣ ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ የተቀበረበት፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር 3 ወር ከ10 ቀናት የተቀመጠችበት ገዳም ነው። ቅዱስ ያሬድ ምልክት የሌለውን ድጓ የጻፈባትና መጽሐፉና መስቀሉ የሚገኝበት ገዳም ነው። 👉ዳጋ እስጢፋኖስ፦ ዳጋ እስጢፋኖስ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በአቡነ ሒሩት አምላክ የተመሠረተ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ ውኃ ዘመን የሰው ዘር በኖኅ መርከብ አማካይነት መዳኑን ለማመልከት በመርከብ ቅርፅ የተሠራ ነው። ✔️የዐፄ ዳዊት (1374-1406 ዓ.ም)፣ ✔️የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም)፣ ✔️የዐፄ ሱስኒዮስ (1600-1625 ዓ.ም.) እና ✔️የዐፄ ፋሲል (1625-1660 ዓ.ም) አስክሬን ሳይፈርስ በክብር የሚገኘው በዚሁ ገዳም ነው። ደብረ ማሪያም ገዳም የደብረ ማርያም ገዳም በጣና ዘጌ ባሕረ ገብ መሬት ይገኛል። ገዳሙ በጣና ሀይቅ ላይ ከሚገኙት አንጋፋ ገዳማት አንዱ ሲሆን የተለያዩ የብራና መጻሕፍት የሚገኙበትና የውስጠኛው ክፍል በአሮጌ ሙሪያል ሥዕሎች ያጌጠ ክብ ቅርጽ ያለው ባህርዳርን ለሚጎበኙ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ነው ። በጣና ሀይቅ ላይ ከሚገኙ ገዳማት መካከል ደብረ ማርያም አንዷ ነች፡፡ ደብረ ማርያም የተመሠረተችው በ12ኛው ክ/ዘመን እንደሆነ ከገዳሙ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል፡፡ የመሰረቱት አቡነ ታዲዮስ ሲሆኑ ገዳሟን ልዩ የሚያደረጋት በአባይ ራስ ላይ መገኘቷና በአካባቢው ብዛት ያላቸው ጉማሬዎች የሚገኙበት አካባቢ በመሆኑ አንዳንዴ ጉማሬ በመባል ይጠራል፡፡ የገዳሟ ልዩ ቅርስ ከ7ዐዐ አመት በላይ የሆነው የሽክላ ነጋሪት ሲኖር የአቡነ ታዲዎስ የአጅ መስቀል እና ልዩ ልዩ የብራና መፅሀፍት ይገኛሉ፡፡ ደብረ ማርያም ከከተማዋ ከ1ዐ-15 ደቂቃ የጀልባ ጉዞ ርቀት ላይም ትገኛለች፡፡ እነዚህና ሌሎች በርካታ ደሴቶችንና የሀይቁን ዙሪያ መሰረት ያደረጉ ጥንታዊ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ገዳማትና ጥንታዊ ቤተክርስቲያናት ለጎብኝወች ማራኪና አይረሴ ጊዜን እንዲያሳልፉ ያደርጋሉ፡፡ 👉ባህር ዳር ገበያና የገበያ ማዕከላት፦ የባህርዳር ከተማን የእለት እለት እንቅስቃሴ መስተጋብርና የግብይት መለዋወጫ ማዕል እንዲሁም ቱሪስት መዳረሻዎች መካከል በከተማ መሐል የሚገኙ የገቢያ ማዕከላት ናቸው። በእነኝህ ማዕከላት በርካታ ለአይን ማራኪ የሆኑ ሁነቶችን የምንመለከትባቸው ናቸው:: በተለይም በርካታ የባህላዊና የጥበብ ውጤቶች የሚገኙት በእነኝህ ማዕከላት ነው። ከእነዚህ መካከል የአንበሳ ጥበብ ጋለሪ አንዱ ሲሆን ሌሎች የተለዩ የባህል ማዕከላት ይገኛሉ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በከተማዋ እምብርት የሚገኝ አስደናቂ እይታ ያለው ቤተክርስቲያን ነው። የጣና ሀይቅን በቅርብ ማግኘት ይቻላል:: በሌላ በኩል ቆይታችንን የበለጠ ሳቢና አስደሳች እንዲሁም አይረሴ ለማድረግ በውቢቷ ባህርዳር ቆይታችን ወቅት ልናከናውናቸው የሚገቡ ሌሎች መዝናኛዎች፦ 👉በጣና ሀይቅ የጀልባ ጉዞ፦ የጣና ሀይቅ የኢትዮጵያ ትልቁ ሀይቅ ሲሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ የጀልባ ጉዞ ካደረጉ፣ ወንዙ ከሐይቁ ወደሚፈስበት ቦታ እንዲወስድዎት “ሹፌሩን” ይጠይቁ። በጣም አስደናቂ የተፈጥሮ ቅንብር ይመለከታሉ። ምናልባትም ጉማሬዎች በሀይቁ ላይ ሲገማሸሩ ለመመልከት በጣም ጥሩ ቦታ ነው፡፡ እንዲሁም ወደዚህ ቦታ በብስክሌት መድረስ ይችላሉ ፣ ከተማዋን ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ትተው ከድልድዩ በኋላ ወደ ግራ በመታጠፍ በኮብልስቶን መስመር ላይ። ብዙ አዕዋፍና ከብቶች የሚሰማሩበት አረንጓዴ አካባቢ እስክትደርሱ ድረስ 1ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ያህል በመጓዝ የአባይ ወንዝ የጣና ሀይቅን ለቆ ሲወጣ ድንቅ እይታን ይፈጥራል፡፡ 👉ወደ ጭስ አባይ ፏፏቴ፦ የጭስ አባይ ፏፏቴ አማራ ክልል ካሉት ምርጥና ታዋቂ የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዱ ነው፡፡በታላቁ ወንዝ አባይ ወንዝ የጉዞ ሰንሰለት መካከል የሚፈጠር እና ድንቅ ትዕይንት የሚፈጠርበት ቦታ ነው። ይህ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታ የሆነው ጭስ አባይ ፏፏቴ የሚገኘው ከክልላችን ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ከተማ በስተምስራቅ አቅጣጫ በ30 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ነው። በአባይ ወንዝ የጉዞ ሒደት ላይ ግማሽ ማይል ያህል የጎን ስፋት ባለው ከፍታ ቦታ ላይ ከላይ ወደ ታች ከ37 እስከ 45 ሜትር ወይም 150 ጫማ አካባቢ የሚወነጨፈው ሲሆን የጢስ አባይ ፏፏቴ የውሀ ፍሰት ላየው ቀልብን የሚማርክ ድንቅ የተፈጥሮ መስህብ ነው፡፡ ይህ ድንቅ ፏፏቴ በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንደሆነ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና የተፈጥሮ ሐብት ባለሙያዎች ጽፈዋል። በአካባቢው ከጢስ አባይ ፏፏቴ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ በርካታ የእጽዋትና የዱር እንስሳት መገኛም ጭምር ነው። የቦታ መልካ ምድሩ አቀማመጥ ውብና ማራኪ ነው። በታችኛው የፏፏቴው ክፍል የሚገኘው እና እንደ እ.ኤ.አ በ1626 በንጉስ ሱሲንዮስ በኢትዮጵያ ለመጀመሪ ጊዜ የተገነባው በተለምዶ የፖርቹጋሎች ድልድይ ተብሎ የሚጠራው የድንጋይ ድልድይ ለቱሪስቶች ተጨማሪ መስህብ ቦታ ነው፡፡ 👉የዘጌ ባሕረ ገብ መሬትን ይጎብኙ፦ ከጣና ሀይቅ ደቡብ ምዕራብ ዳር የሚገኘው ዘጌ ባሕረ ገብ መሬት የበርካታ ገዳማት መኖሪያ ሲሆን ብዙዎቹ በጥሩ ሁኔታ የተጠበቁ፣ አስደናቂ ውበት ያላቸው ሥዕሎች ያሏቸው ናቸው። 👉የስጦታ እቃዎችን ይግዙ፦ ባህር ዳር በየእለቱ ክፍት የሆነ ግዙፍና በቀለማት ያሸበረቀ ገበያ አላት። በገበያው ብዙ ከውጭ የሚገቡ ቁሳቁሶች የሚገኙ ሲሆን፣ ነገር ግን የሚያማምሩ የአካባቢ ጨርቆችን፣ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመማ ቅመሞችን እና ጣፋጭ የኦርጋኒክ ማርን ማግኘት ይችላሉ። የአካባቢው ልዩ ባለሙያ የሰሯቸው በፍየል ቆዳ የተሸፈኑ ትናንሽ መቀመጫዎች በጣም ማራኪ ናቸው፡፡ 👉ማራኪ የምሽት ህይወትን በባህርዳር ያሳልፉ፦ በባህር ዳር በርካታ ሬስቶራንቶችና ደረጃቸውን የጠበቁ ክለቦች፣ የምሽት መዝናኛወችና መናፈሻወች በብዛትና በጥራት የሚገኙባት ከተማ ስትሆን በከተማዋ ሀገራዊ ምግብና መጠጥ እንዲሁም የውጭ ምግብና መጠጦች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መዝናናት እጅግ አስደሳች ነው፡፡ በተለይም በከተማዋ የእግር ጉዞ እያደረጉ ለመዝናናት ተስማሚ እይታና ምቹ የአየር ንብረትን የተጎናጸፈች ናት። 👉በጣና ሐይቅ ላይ ያለው የአእዋፍት ትእይንት፦ የኢትዮጵያ ጌጥ በመባል የሚታወቀው ጣና ሀይቅ የሀገሪቱ ትልቁ ሀይቅ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ በአፍሪካ፣ በእስያ እና በአውሮፓ መካከል ለሚጓዙ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ስደተኛ የወፍ ዝርያዎች ጠቃሚ ቦታ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። አካባቢው በአብዛኛው ጎብኝዎች አንደበት እንደሚገለፀው የምድር ገነት ይሉታል ፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ የአዕዋፍ ዝርያዎች ውስጥ ከ900 የሚበልጡ የወፍ ዝርያዎች በዚህ አካባቢ ይገኛሉ። 👉የፖርቹጋል ድልድይን ይጎብኙ፦ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት እጅግ ማራኪ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእንቁላል እንደተገነባ የሚነገረው ድልድይ ሲሆን ድልድዩ ከጭስ አባይ ፏፏቴ የታችኛው አካል ላይ ይገኛል። 👉ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፦ ባህር ዳር በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከመሀል ከተማ በስተምዕራብ 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ከአዲስ አበባ መደበኛ በረራዎች አሉ ። ወደ ላሊበላ ፣ ጎንደር እና ወደተለያዩ ቦታዎች የሚሄዱ የሀገር ውስጥ በረራዎችን ያስተናግዳል። 👉የባህርዳር የየብስ ትራንስፖርት አማራጮች። ባህርዳ አራት ዋና ዋና መውጫ በሮች አሏት። ✔️ባህርዳር ማርቆስ አዲስ አበባ፣ ✔️ባህርዳር ሞጣ አዲስ አበባ፣ ✔️ባህርዳ ቁንዝላ ሻውራ ደለጎ፣ ጎንደር ✔️ባህርዳር ጎንደርና ደብረታቦር በሮች ይገኙበታል። 👉በውቢቱ ባሕርዳር ከጥር እስከ ጥር፦ ✔️የጥምቀት በዓል፣ ✔️የጀልባና ታንኳ ቀዘፋ ትርኢት/ወድድር፣ ✔️ሽርሽ በባይስክል፣ ✔️ሰባሩ ጊዮርጊስ፣ ✔️አስተሪዮ ማሪያም፣ ✔️የገቢ ማሰባሰቢያ የሩጫ ውድድርና ✔️የኤግዚቢሽን ባዛር ✔️እንዲሁም በተለያዩ ሁነቶች ደምቃና ተውባ እንግዶቿን ትጠብቃችኋለች። 👉ይምጡ ጥርን በባሕር ዳር ይታደሙ‼️ ተደስተው ይመለሳሉ! #ጥርንበባህርዳርአይቀርም #ሽርሽርበብስክሌትበባህርዳርበ14 #visitbahirdarcity #bahirdarcitycommunication #ጥምቀትን #Ethiopia #VisitAmhara ዘገባው የባህርዳር ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ነው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply