ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዲዝን አሰናበተ ! የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በዛሬው ዕለት ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል። የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/AwPOm3wFFUDr5gD389ZZzdkOaGIp1e3kmxLCw0lbXNDVUOlvseuMpXcR0j5Sr5RGKm5V0F0ZK9S68S_ydI3a6-DnET0k_RI8wBzeZTdTFwW4EAsxdObnxzdRIg6up3EbZPCUFtjwrs8XYbgNc0B2oxrxMRPTal8P83sM3p4DokO2-he_mBjjjAQj7SPK-EmLT1Dow0ArrEAwGbgXzFhguMgmZ301DR6sAvxKbADbQ_bDjPsoX7y3if88Leu4i6zGqIJE13ENBVSRPRjBmszfUyIiip_V0i0a6jOYj19-O1qlHqc2GakDmw1vtuGIwW8qcPiUxHrRq42KaNY5psVNbA.jpg

ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዲዝን አሰናበተ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በዛሬው ዕለት ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።

የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በዛሬው እለት ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደተነጋገሩ እና ውሳኔውን እንዳሳወቁ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ዣቪ ከወራት በፊት በአመቱ መጨረሻ ባርሴሎናን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ክለቡ ሀሳባቸውን አስቀይሯቸው ለመቆየት ወስነው እንደነበር አይዘነጋም።

አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታቸውን እሁድ ከሲቪያ ጋር በሚደረግ መርሐ ግብር እንደሚመሩ ተገልጿል።

ዣቪ ሀርናንዴዝ ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት እየመሩ ባለፈው አመት የላሊጋውን ዋንጫ ማሳካት ችለዋል ።

በቀጣይ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ፊሊክ ባርሴሎናን በሀላፊነት ይረከባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

በ ጋዲሳ መገርሳ

Source: Link to the Post

Leave a Reply