ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት በከተማዋ ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች የሰው ህይወት አለፈ። በአዲስ አበባ ቅዳሜ ምሽት ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ መድረሱን የእሳ…

ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት በከተማዋ ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች የሰው ህይወት አለፈ።

በአዲስ አበባ ቅዳሜ ምሽት ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ቅዳሜ ምሽት በቦሌ ክፍለ -ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ ቺቺኒያ ይልማ ስጋቤት ፊትለፊት በተነሳ የእሳት አደጋ፣ በመንገድ ዳር ቆመዉ የነበሩ አንድ ላዳ ታክሲና አንድ የቤት አዉቶሞቢል የተቃጠሉ ሲሆን በሰዉ ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።

የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በእሳት አደጋዉ የኤሌክትሪክ ትራንሰፎርመር ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ብርጭቆ ማርያም እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ፣ የቤት አዉትሞቢል ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ የሰው ህይወት ማለፉን አቶ ንጋቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

አደጋው በደረሰበት ወቅት በተሽከርካሪዉ ዉስጥ ከነበሩ ሰዎች መካከል አንድ ዕድሜዉ 36 ዓመት የሆነ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወቱ ያለፈዉን ግለሰብ አስከሬን ግጭት ከአጋጠመዉ ተሽከርካሪ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውን የተናገሩት ባለሙያው የትራፊክ አደጋዉን ዝርዝር ጉዳይ ፖሊስ እያጣራ ይገኛል ሲሉ ብለዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply