ባስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ በትግራይ ያለው የረሀብ አደጋ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።አቶ ጌታቸው በተመ የሕጻናት መርጃ ድር…

ባስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ በትግራይ ያለው የረሀብ አደጋ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።

አቶ ጌታቸው በተመ የሕጻናት መርጃ ድርክት UNICEF የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ አካባቢ ዳይሬክተር ኤትሌቫ ካዲሊ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ ባለፉት አስር ወራት የምግብ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት ያንዣበበውን አስከፊ ሰብአዊ እልቂት ለመቀልበስ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የ10 ወራት እገዳው ያስከተለውን ከፍተኛ ጉዳት በማመልከት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።

በክልሉ የምግብ እርዳታው መቋረጡን በመቶ ሺህዎች ላይ የተበየነ «የሞት ቅጣት» ነው ያሉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ዘግይቶ የሚቀርብ ማንኛውም እርዳታ በኋላ ትርጉም አልባ እንዳይሆን ያላቸውን ስጋት መግለጻቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ኤትሌቫ ካዲሊ በበኩላቸው በክልሉ  የድርቅ ሁኔታ መባባሱ አሳሳቢ መሆኑን በማረጋገጥ፤ አስቸኳይ እርምጃ ተወስዶ ለሕጻናትም ሆነ ለማኅበረሰቡ የምግብ እርዳታ ካልደረሰ መዘግየቱ የከፋ ጠኔ ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።

ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply