ባቡሮች በየፌርማታው የሚደርሱበትን ጊዜ ለማሳጠር መስመር ላይ የሚገኙ የመንገደኛ እና የመኪና ማቋረጫዎችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ

ባቡሮች በየፌርማታው የሚደርሱበትን ጊዜ ለማሳጠር መስመር ላይ የሚገኙ የመንገደኛ እና የመኪና ማቋረጫዎችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባቡሮች በየፌርማታው የሚደርሱበትን ጊዜ ወደ 6 ደቂቃ ለማሳጠር መስመር ላይ የሚገኙ የመንገደኛ እና የመኪና ማቋረጫዎችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ተፈራ እንደገለጹት፣ ለባቡር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የተቀላጠፈ እና ተመራጭ አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት በቀን ከ120 ሺህ በላይ ዜጎችን ሲያጓጉዝ ነበር ያሉት ስራ አስኪያጁ፣ በአሁኑ ወቅትም ከ88 ሺህ እስከ 90 ሺህ የሚደርሱ ተጠቃሚዎችን በቀን ያሥተናግዳል ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት፣ የባቡር ሃዲድ እና ኬብል ስረቆት እንዲሁም የበጀት እጥረት ፕሮጀክቱ ከዚህ የተሻለ አገለግሎት እንዳይሰጥ ያደረጉ ተግዳሮች መሆናቸውን አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ አጠቃላይ ካሉት 41 ባቡሮች ውስጥ 29 የሚደርሱት ብቻ አገልግሎት እየሠጡ መሆኑን ስራ አስኪጁ አክለዋል፡፡

በእነዚህ ባቡሮች እና አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ መሰረት ልማትም ባቡሮች በ10 ደቂቃ ውስጥ በየፌርማታው በመድረስ ተጠቃሚዎችን እያጓጓዙ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ባቡሮቹ በየፌርማታው የሚደርሱበትን ጊዜ ወደ 6 ደቂቃ ለማሳጠርም በመስማር ላይ የሚገኙ የመንገደኛ እና የመኪና ማቋረጫ መንገዶችን አስወገዶ በድልድይ መተካት አሊያም የባቡሮችን ቁጥር መጨመር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የማቋረጫ መንገዶችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮፖዛል ማስገባታቸውን የገለጹት አቶ ሙሉቀን ፣ የከተማ አስተዳደሩም የመዲናዋን የትራንስፖር ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ የባቡሮችን ቁጥር በመጨመር አገልግሎቱን ፈጣን እና ተመራጭ ለማድረግ ከፌዴራል መንግስት ጋር በቅንጅት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

በመላኩ ገድፍ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ባቡሮች በየፌርማታው የሚደርሱበትን ጊዜ ለማሳጠር መስመር ላይ የሚገኙ የመንገደኛ እና የመኪና ማቋረጫዎችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply