ባንኩ በባለፈው በጀት ዓመት 9.8 ቢሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉን አስታውቋል፡፡አዋሽ ባንክ በባለፈው የ2015 በጀት አመት 9.8 ቢለዮን ብር ማትረፍ መቻሉን ያሳወቀ ሲሆን ይህም በግል ባንኮች…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/SZJ8yubS9hweSNZ8P885gB-R3LhHH_oazbQfen32f_3DATmwBWHdaV2XUEQJLo_ZQCpfcLJR-XvuXA7E4r_nM9I3wwAK87dCtif6jtug1EK4Siz1VsJo4g8pWbrz5KwPMG2RXlJZ0PN5Rru4xdmNh3s2MuGWUcWRP0t89rFihjpb8v3SFZU6wId9nvvmQeEfFtyYg0UxoB0rccuAQfU0PN7jsSMhrTyHel9XVfwHtrM0Ez5Ii0FYcLqXqIp5THfq6r7NFgFWSvjcRp-SpOrMa8cohLs7YiRI0xYQcchcdHkKQrAq2oiyw1GoVu66Pu05E_tHpm08orSszhgmcRk_Qg.jpg

ባንኩ በባለፈው በጀት ዓመት 9.8 ቢሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉን አስታውቋል፡፡

አዋሽ ባንክ በባለፈው የ2015 በጀት አመት 9.8 ቢለዮን ብር ማትረፍ መቻሉን ያሳወቀ ሲሆን ይህም በግል ባንኮች ታሪክ ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

ባንኩ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው እለት ባደረገው የባለአክሲዮኖች 28 ጠቅላላ ጉባዬ ላይ ነው፡፡

አዋሽ ባንክ የባንክ ዘርፉን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እያሳደገ ይገኛል ያሉት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉሬ ኩምሳ ይህም ባንኩን ውጤታማ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም ባንኩ 9.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኛቱን የገለጹ ሲሆን ፤ከቀደመው የበጀት አመት ጋር ሲነጸጸር ፤የ2.3 ቢሊዮን ወይም የ31 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል፡፡

በብድር ረገድ በበጀት አመቱ 40.9 ቢሊዮን ብር ለተለያዩ ክፍላተ ኢኮኖሚዎች የተሰጠ ሲሆን ፤በአጠቃላይ ለኢኮኖሚው ዘርፍ በብድር መልክ የተሰጠውን የብር መጠን ወደ 224 ቢሊየን ማድረስ መቻሉን አንስተዋል፡፡

አዋሽ ባንክ አዲስ ባስጀመረው ፕሮጀክትም በተደረገ ውድድር ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት ማድረጉን የገለጹት አቶ ጉሬ ኩምሳ ለስራ ፈጣሪዎች ያለምንም የብድር መያዣ 5 ሚሊየን ብር ብድር ሰጥቷል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በ2014 ዓ.ም ከነበረበት 10.2 ቢሊዮን ብር በ2015 ዓ.ም ወደ 14 ቢሊዮን ብር ያሳደገ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ የሃብት መጠን 224 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ አለም አቀፋዊ በሆኑ እና ሃገሪቱ ውስጥ እየተፈጠሩ ባሉ ግጭቶች ሳይበገር በአስር አመቱ ፍኖተ ካርታው ላይ ባስቀመጠው ስራቴጂ በመመራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

Source: Link to the Post

Leave a Reply