ባንኩ የእርሻ ግብአቶች ግዥ ክፍያን በሲቢኢ ብር መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

ባንኩ የእርሻ ግብአቶች ግዥ ክፍያን በሲቢኢ ብር መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእርሻ ግብአቶች ግዥ ክፍያን በሲቢኢ ብር መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከግሪን አግሮ ሶሉሽን ከተባለ ድርጅት ጋር ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ የሲቢኢ ብር አገልግሎትን ከግሪን አግሮ ሶሉሽን ‘ለእርሻ’ የተሰኘ መተግበሪያ ጋር በማጣመር አርሶ አደሮች የዘር፣ ማዳበሪያ፣ ፀረ-ተባይ እና ፀረ-አረም ኬሚካሎች ግዥ ክፍያን በሲቢኢ ብር አማካኝነት በቀላሉ መፈፀም ያስችለዋል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዮሀንስ ሚሊዮን በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሚጀመረው አገልግሎት ባንኩ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ ዘመናዊ የክፍያ ስርዓትን ለመዘርጋት እየሠራ ያለው ተግባር አካል ነው ብለዋል፡፡
አገልግሎቱ አርሶ አደሩ ወደባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ጥሬ ገንዘብ ማውጣትና መገበያየት ሳያስፈልገው ባለበት አካባቢ በቀላሉ ክፍያውን በመፈጸም የግብርና ግብአቶችን መግዛት እንደሚያስችለው አቶ ዮሀንስ ገልጸዋል፡፡
ግሪን አግሮ ሶሉሽንን በመወከል በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሐም እንድሪያስ በበኩላቸው በተደራሽነቱና በቴክኖሎጂ በታገዘ አገልግሎቱ በላቀ ደረጃ ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የፈጸሙት ስምምነት የግብርና ግብአቶች ስርጭትን ለማቀላጠፍ እየሠሩ ያለውን ሥራ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርግላቸው ገልፀዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን አህመድ በበኩላቸው በስምምነቱ መንግስት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፖሊሲ በመቅረጽ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀው የግብርናውን ዘርፍ ዲጂታላይዝ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ መናገራቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

The post ባንኩ የእርሻ ግብአቶች ግዥ ክፍያን በሲቢኢ ብር መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply