ባይደንና ፑቲን ዛሬ ይነጋገራሉ

https://gdb.voanews.com/B602E561-995B-4DC9-A36E-FA2487AF4ABD_w800_h450.jpg

ሩሲያ ወታደሮችዋን በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ማከማቸቷ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ፕሬዚዳንት ባይደንና እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን ዛሬ ማክሰኞ በድረ ገጽ ተገናኝተው ይነጋገራሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ሩሲያ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት አካል የነበረቸውን ትንሿ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ ጠንካራ የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ መጣልን ጨምሮ ሌሎች እምርጃዎችን ሊወስዱ እንደሚችሉ ያስጠንቀቅዋቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲምትሪ ፔሽኮቭ ባላፈው ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የዩናይትድ ስቴት ና የሩሲያ ግንኙነት ያለበት ሁኔታ በመጥፎ ደረጃ ይገኛል ካሉ በኋላ ለማንኛውም ክሬምሊን ፕሬዚዳንት ባይደን የሚሉትን ነገር ለመስማት ተዘጋጅታለች ብለዋል፡፡

በሌላም በኩል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአውሮፓውያን አጋሮቻቸው ጋር ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ስለምታደርገው ወታደራዊ የጦር ክምችት በስልክ ተገናኝተው ለመማከር አቅደዋል ሲል አሶሼይትድ ፕሬስ ትናንት ዘገቦ ነበር፡፡

ይህ የሚሆነው ባይደን ዛሬ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን ጋር ለመነጋገር ካቀዱበት አንድ ቀን በፊት ነው፡፡ ከባይደን ጋር  በስልክ በሚደረገው ውይይት ተገኘተው ይማከራሉ ከተባሉት የኔቶ አባል አገራት መካከል እንግሊዝ ፈረንሳይና ጀርመንና ጣልያን  መሆናቸው ተዘግቧል፡፡ 

የዩናይትድ ስቴትስ የመረጃ ባለሥልጣናት ሩሲያ ወደ 70ሺ የሚጠጉ ወታደሮችዋን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷን ይናገራሉ፡፡

ባይደን ፑትኒን ካነጋገሩ በኋላ በቅርቡ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር እንደሚነጋገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply