ባይደን በ1ትሪሊዮን ዶላር የመሰረት ልማት በጀት ላይ ፈረሙ

https://gdb.voanews.com/0CEA19DA-02B0-4136-8270-32FD57546B11_w800_h450.jpg

ፕሬዚዳንት ባይደን በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ያለውን የመሠረተ ልማት ግንባታ ያሻሽላል የተባለውን የአንድ ትሪሊዮን ዶላር የበጀት ዕቅዳቸውን ትናንት ሰኞ በዋይት ኃውስ በተካሄደ ሥነ ስርዓት ፈረመው አጽድቀዋል፡፡

ግዙፉ የወጭ በጀት፣ የተበላሹና ያረጁ መንገዶችና ድልድዮችን፣ የባቡር መስመሮችን የሚያድስና አዳዲስ የህዝብ ትራንስፖርት መገለገያዎችን፣ እንዲሁም የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት አገልግሎቶችን ያስፋፋል ተብሏል፡፡

ሥነ ስርዓቱ ላይ የዴሞክራትና የሪፐብሊካን አባላት እንዲሁም ከየክፍለ ግዛቱ የመጡ የክፍለ ግዛት ገዥዎች፣ ከንቲባዎችና የሠራተኛ ማህበራት መገኘታቸው ተነግሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply