ባይደን በ768 ቢሊዮን ዶላር መከላከያ በጀት ላይ ፈረሙ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትናንትናው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ በጀት 768.2 ቢሊዮን ዶላር እንዲሆን በሚያዘው ረቂቅ ላይ በመፈረም ህግ ሆኖ እንዲወጣ አጽድቀዋል፡፡ 

ህጉ እኤአ በ2022 ለሠራዊቱ አባላት የ2.7 ከመቶ የደመወዝ ጭማሪ እንዲሰጥ የሚያዝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ 

የዩናይትድ ስቴትስ መከካለያ በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ5 ከመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ተገልጿል፡፡ 

የበጀት ረቂቁ በዲሞክራትና የሪፐብሊካን ህግ አውጭ የምክር ቤት አባላት ብርቱ ክርክር ሲካሄድበት የቆየ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ከበጀቱ ህጉ ጋር ተያይዞ፣ ለሠራዊቱ አባላትና ቤተሰቦቻቸው የሚሰጠው ጥቅማ ጥቅምና የተቀላጠፈ የፍትህ አገልግሎት እንዲሁም የአገሪቱን የመከላከል አቅም ታሳቢ ያደረጉ ሥልጣኖችን ያጎናጸፉ ውሳኔዎች የተካተቱበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply