ባይደን የኬንያን ፕሬዚዳንት በዋይት ሀውስ ያነጋግራሉ

https://gdb.voanews.com/F3A22F79-E2E9-429B-B9C0-DBFD6ED7613D_w800_h450.jpg

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳን ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ነገ ሀሙስ በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፡፡ 

ባይደን በፕሬዚዳንትነት ዚያቸው አንድን የአፍሪካ አገር መሪ ተቀብለው ሲያነጋግሩ የመጀመሪያቸው ይሆናል፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ባወጡት መግለጫ ሁለቱ መሪዎች “ዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን በመክላከል ሰላምና ደህንነትን ማስከበርና የምጣኔ ሀብት እድገትን በማምጣት እንዲሁ የከባቢ አየር ለውጥ” ዙሪያ ይነጋገራሉ ብለዋል፡፡

ኬኒያ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የወቅቱ ተረኛ ፕሬዚዳንት ነች፡፡

ሁለቱ አገሮች የሚገናኙት ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ ማእቀብ ለመጣል በምታሰላስልበት ጊዜ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply