ቤተክርስቲያኗ የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል አለች፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል ብላለች፡፡ቤተክርስቲያኗ ይህንን ያለችው ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/JA7-VcGBn-xu119mURRLInv5PInJ7D4Woo3N0hxial0-T6zlZTvss6seeTqiZU2iunOOLmxbXrKQa6r4J70_DhW2xtJ8SBv2w-93UQhdDpfrn_kfD1uO0t6FpefVSEjW4cY2wcQTS0BaehNVrrYMpXcDqytey5gTGyUl8OxrqYHW3kS8hW7ny411f2dLVnZ28OsFsqy03txVtGgKi2aj9xiyn89JZqtsyqbMLOSBeE_nagvPXh5fFe_mW1WFUljSmjC758FsNcHWsGVONwO830c0LvkM_SXSojOvgS5Io4B1z9kZJCFDZEaWde9dmzPXtO3ay8ltNPrEUadn0VSn_g.jpg

ቤተክርስቲያኗ የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል አለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል ብላለች፡፡

ቤተክርስቲያኗ ይህንን ያለችው ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋልም ብለዋል፡፡

ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ .ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply