
እስራኤል ውስጥ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከተመዘገቡት የዘረኝነት ጥቃቶች ግማሽ ያህሉ ቤተ-እስራኤላውያን እንዲሁም አረቦች ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ በመንግሥት የወጣ ሪፖርት አመለከተ። የእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ባወጣውን ሪፖርት መሠረት እንደ አውሮፓውያኑ በ2021 እስራኤል ውስጥ ከተፈጸሙ 458 ዘር ተኮር ጥቃቶች መካከል 48 በመቶው ያህሉ የደረሱት ከኢትዮጵያዊ በሄዱ ቤተ-እስራኤላውያን እና በአረቦች ላይ ነው።
Source: Link to the Post