You are currently viewing ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና_ሚስት ትላንት ማታ በጥይት ተመተው  ተገድሉ።          ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም                  አሻራ ሚዲያ ፣ በሰበታ ከተማ በኬንተሪ  ደረ…

ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና_ሚስት ትላንት ማታ በጥይት ተመተው ተገድሉ። ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረ…

ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና_ሚስት ትላንት ማታ በጥይት ተመተው ተገድሉ። ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንትበስቲያ ነበረ። ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛ ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት የሆነው ነዉ። ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መሀከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በሆላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ትላንት ከሰአትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ፊኒሽጉ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ ግራወንዱ ላይ ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ “ቤት እስክታገኙ እዛ ግቡ” ብሎዋቸዉ ገቡ። ማታ ፖሊሶች መጥተው እነመሀመድ የተኙበትን የህንፃውን ግራወንድ በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ። በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመቱ ። ጩኸቱን ሰምታ ከመጡት ጎረቤቶች መሀል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል። በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply