ቤታችን ያለአግባብ ፈርሷል ያሉ አካል ጉዳተኞች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን…

ቤታችን ያለአግባብ ፈርሷል ያሉ አካል ጉዳተኞች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት መከናወን አለበት ሲልም አሰመኮ አስታውቋል፡፡

ግንት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከ አስራአንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ 160 በላይ አካል ጉዳተኞች በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው ቅሬታ ማሰማታቸውን ኮምሽኑ ለኢትዮ ኤፍኤም ገልፃል፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ካለው የንግድ ቤቶች የማፍረስ ሂደት ጋር በተገናኘ የንግድ ቤቶቻቸው ያላግባብ እንዲፈርሱ መደረጉን፣ ንብረታቸው መወሰዱን እንዲሁም ቅሬታቸውን ለማቅረብ በሄዱባቸው የመንግሥት ተቋማት በጸጥታ አካላት ማዋከብ እና እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን ለኮሚሽኑ አስረድተዋል ሲሉ የኮምሽመኑ ባወጣው መግለጫም አስታውቋል።

የኢሰመኮ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ ኮሚሽኑ ቅሬታቸውን ተቀብሎ የክትትል እና የምርመራ ሥራዎችን በአፋጣኝ እንደሚጀምር እና ግኝቶቹንም እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል።

ኮሚሽነር ርግበ አክለውም ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለው የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና እርምጃው በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።

የውል ሰው ገዝሙ

ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply