ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ተማሪዎች ትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳልሆኑ ተገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ሳብያ በዚህ ዓመት ከ69ሺ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ “ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ያልተመለሱት ታጣቂዎች ከ100 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችን በማውደማቸው ነው” ብለዋል።

ተማሪዎቹን ወደ ትሞህርት ገበታቸው ለመመለስ የክልሉ መንግሥት ጥረት እያደረገ ቢሆንም፤ የሚመለሱበት ጊዜን ለመወሰን ግን አዳጋች ነው ሲሉ ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply