ብሄራዊ መታወቂያ ያላገኘ ሰው የማህበራዊ አገልግሎት አያገኝም በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡የብሄራዊ መታወቂያን የያዘ ማንኛውም ማህበረሰብ የትኛዉንም አገልግሎት እና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/PUMGEivjeZWbv1cq2wXSNqiOkbYGP_0dKKUJFk7doUj33tRUpcFqOvOjdf9pdt2Ufhc5-rJnoua5SMqrEX0MI8gHks1DqbdOi6cFJR5wHT0XR-7iiHJkUXhRiRW7iPa-aK7EyhmugDAkSli-NSM6avwUbpxUu4-cARr4WIvhC_dCRznW9PtG6sE1NLax6lbWLGNlojExIrSk4y0KFmk1orSDd5TkoWzOKSwez_oAZ4Il7P6XsqKfkbm2nh3mM-sIJC2g11ozQS-JCvq_9zSrhJNhfOAypAf8At3Yp-5ZkWt42_orTD7cfjRi-GcDjvCk5l41M5igPpFj0Q_rCSdEyw.jpg

ብሄራዊ መታወቂያ ያላገኘ ሰው የማህበራዊ አገልግሎት አያገኝም በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የብሄራዊ መታወቂያን የያዘ ማንኛውም ማህበረሰብ የትኛዉንም አገልግሎት እና ማንነቱን ማረጋገጥ የሚፈልግበት አገልግሎት ላይ መጠቀም እንደሚችሉ ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የብሄራዊ መታወቂያ ኮሚንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ይሄንን መታወቂያ እንደ አንድ የአገልግሎት አማራጭ አድርገው ይጠቀሙበታል ማለት እንጂ፣ ማህበረሰቡ ብሄራዊ መታወቂያ ከሌለው ምንም አይነት አገልግሎት አያገኝም ማለት እንዳልሆነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከሶስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ሰው የብሄራዊ መታወቂያን ለማግኘት ምዝገባ እንዳከናወነ ታውቋል።

የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አቤኔዘር፣ማህበረሰቡ ስለብሄራዊ መታወቂያ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛው ምንጭ ማግኘት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በሀመረ ፍሬው

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply