ብሄራዊ ማህበረሰብ ተኮር ምክክር ዛሬ በመላው ሀገሪቱ ተጀመረ

ብሄራዊ ማህበረሰብ ተኮር ምክክር ዛሬ በመላው ሀገሪቱ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰላም ሚኒስቴር አመቻችነት ከዛሬ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ማህበረሰብ ተኮር የምክክር መድረኮች ተዘጋጅተው ሂደቱ በይፋ ተጀምሯል፡፡
ይህ ብሄራዊ ማህበረሰብ ተኮር ምክክር ሂደት በአካባቢያዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከቤተሰብና መንደር አንስቶ መላው ማህበረሰብ በየደረጃው ስልጡን ምክክር በማድረግ የጋራ አረዳድ እና ብሔራዊ መግባባት የሚመጣበትን መንገድ ለማመቻቸት ያለመ ነው ተብሏል።
ከዚህ ሀገር አቀፍ የማህበረሰብ ምክክር ከሚጠበቁ በርካታ ውጤቶች መካከል ስልጡን፣ ምክንያታዊና ሞጋች ማህበረሰባዊ የአስተሳሰብ ልዕልና፤ የሚያጋጥሙ ችግሮች ስልጡን በሆነ መንገድ በራሱ የሚፈታ እና ቀጣይነት ያለው እድገት የሚያረጋግጥ ማህበረሰባዊ አቅም ማሳደግ ከሚጠበቁ ውጤቶች ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም በሰለጠነና በተቀናጀ መንገድ በአካባቢው ሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ የሚሳተፍ ማህበረሰብ፤ ግለሰብ ከራሱ ጋር፣ ቤተሰብ በውስጡ፣ በማህበረሰብ መካከል እና ማህበረሰብ በተዋረድ ካሉ አገልግሎት ሰጪ አካላት ጋር በጽኑ በመተማመን ሀገርን በክብር ማቆምና የህዝቦችን ዘመን ተሻጋሪ የጋራ እሴቶችን ማሳደግ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለዚህ ሀገራዊ ተግባር ስኬታማነት ሁሉም የየድርሻውን አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ሰላም ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ብሄራዊ ማህበረሰብ ተኮር ምክክር ዛሬ በመላው ሀገሪቱ ተጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply