ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሳት ክትባትን በብዛት እና በጥራት ማምረት እንዲችል ከአውሮፓ ህብረት የማሽን ድጋፍ ተደረገለት

ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሳት ክትባትን በብዛት እና በጥራት ማምረት እንዲችል ከአውሮፓ ህብረት የማሽን ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሳት ክትባትን በብዛት እና በጥራት ማምረት እንዲችል ከ800 ሺህ ዩሮ በላይ በሆነ ወጪ ከአውሮፓ ህብረት የማሽን ድጋፍ ተደረገለት፡፡
ድጋፉ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ሃገራት ክትባቱን ማከፋፈል እንዲቻል ታስቦ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአሁን ወቅት ከ22 በላይ የእንስሳት ክትባት የምታመርተው ኢትዮጵያ ያላትን ትልቅ የእንስሳት ሃብት በሚፈለገው መጠን ምርታማ እንዲሆን የተለያዩ በሽታዎች መኖራቸውን በግብርና ሚኒስቴር የአሳ ሃብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ተናግረዋል፡፡
ይህን ችግር በመቅረፍ ረገድም ማሽኑ ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በ2030 በፍየል እና በግ ላይ የሚከሰተው በሽታ ለማጥፋት ዕቅድ የተነደፈ ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ በ2027 በሽታውን ለማጥፋት ማቀዷ ተገልፆ ማሽኑም ይህን የሚደግፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም አርብቶአደሩ ያለባቸው አከባቢዎች ሞቃት እንደመሆናቸው ሙቀትን መቋቋም የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሳት ክትባትን በብዛት እና በጥራት ማምረት እንዲችል ከአውሮፓ ህብረት የማሽን ድጋፍ ተደረገለት appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply