ብሄራዊ የጥቃት አድርሾች የመረጃ ቋት ለማዘጋጀት በሂደት ላይ መሆኑን የሴቶች ህጻናትና ወጣች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በሀገሪቱ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል ሚኒስቴሩ እየሰራ እደሚገኝ ይታወቃል፡፤ ከዚህም ውስጥ የ10 አመት ፍኖተ-ካርታ ተጠቃሽ ነው፡፡የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከልና ወንጀለኞችን በህግ ተጠቂ ለማድረግ ብሄራዊ የጥቃት አድርሾች የመረጃ ቋት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከጥቃት መከላል ጎን ለጎን የአመራር ድርሻቸው እዲጎላ የምጣኔ-ሀብት ተጠቃሚነታቸው የጎላበት እዲሆንና በራስ መተማመን እዲያዳብሩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሴት ተማሪዎች ጋር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡የሴቶችን ጥቃት መከላከልና ወደ አመራርነት ማምጣት የሚኒስቴሩ ኃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ሁሉም ባድሻዎች ሚናቸውን ሊወጡ እደሚገባ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

***********************************************************************************

ቀን 13/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply