ብሊንከንን ጨምሮ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ቻይና መግባታቸዉ ተገለፀ።

ከሰሞኑን በቻይና እና በታይዋን ማካከል ዉጥረት መባባሱ እየተገለፀ ይገኛል።

ይህ የዲፕሎማቶቹ ጉዞ ከሰሞኑ የዩኤስ ሴኔት ለዩክሬን፣ለእስራኤል እና ለታይዋን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ረቂቅ ህግን ካፀደቀ በኃላ ነዉ።

በትላንትናው ዕለት በቻይናዋ ሻንጋይ ከተማ የገቡት አንቶኒ ብሊንከን ወደ ቤጂንግ ከማቅናታቸዉ በፊት በሻንጋይ ከተማ ከሚገኙ የንግድ መሪዎች ጋር እንደሚገናኙ ተገልፃል።

በቀጣይም ወደ ቤጂንግ ተጉዘዉ ከፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቤጂንግ እና ዋሽንግተን የአሁኑ ጉዞ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ዉይይቶች ማድረግ እና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸዉን ለማጠናከር የታሰበ መሆኑ ገልፀዋል።(አልጀዚራ)

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply