ብሊንከን ሩሲያን በዩክሬን ጉዳይ አስጠነቀቁ

https://gdb.voanews.com/D372355D-6D23-4CF5-92DD-92BA786F40E2_w800_h450.jpg

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሩሲያ አጎራባቿ ዩክሬንን ብትወር የከፋ ነገር ይከታለታል ሲሉ የሩሲያ አቻቸውን አስጠንቅቀዋል፡፡ ብሊንከ ለሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቫሮቭ፣ ሩሲያ ከምስራቅ አውሮፓ ሃገሮችም ጋር ዲፕሎማሲያው መፍትሄዎችን እንድትፈግል ጠይቀዋል፡፡

ብሊንከን ራሺያ ዩክሬንን ብትወር ዩናይትድ ስቴትስ በማያወላዳ መልኩ ምላሹን ትሰጣለች ሲሉ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስዊድን ስቶክሆልም ላይ ከተገናኙ አንድ ቀን በኋላ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሩሲያና ዩክሬን ልዩነቶቻቸን እኤአ በ2014 ባላላቸው የሰላም ሥምምነት መሠረት እንዲያከናውኑ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን ትሰጣለች ብለዋል፡፡

የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲምትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ዩክሬን በሩሲያ ድንበር የምታሳየው ጠብ አጫሪነት እየጨመሩ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ በሰላማዊ መንገድ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗንት ጠቅሰው የዩክሬን ጠብ አጫሪነት ግን ግጭትን የማይቀር ያደርገዋል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply