ብሊንከን ከሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-dc21-08db2618c537_w800_h450.jpg

ትናንት ከከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው የተወያዩት የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ዛሬ ከአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ብሊንከን በትናንት የአዲስ አበባ ቆይታቸው የኢትዮጵያና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት ወደ ነበረበት መልካም ሁኔታ ከመመለሱ በፊት መንግሥት ከህወሓት ጋር የደረሰውን የሠላም ሥምምነት በመተግበር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያሳይ አሳስበዋል።

ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አለመፈጸማችውን ማረጋገጥና ለሁለት ዓመት የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ ሁሉን አካታችና ተአማኒነት ያለው የሽግግር ፍትህ ሥርዓት እንዲፈጠር ብሊንከን ጠይቀዋል።

ሁለት አገሮችን ለመጎብኘት ወደ አፍሪካ ያመሩት ብሊንከን የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀው ዛሬ ወደ ኒዥር አምርተዋል።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply