ብሊንከን ከኬንያው ፕሬዚዳንት ጋር ተነጋገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያና ሶማሊያን ጨምሮ በቀጠናው ባለው የጸጥታ እና የጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ በስልክ መነጋገራቸውን የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጸ፡፡ 

ቃልአቀባዩ ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሁለቱም ወገኖች ግጭቶች እንዲቆሙ፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ ተደራሽነት እንዲኖር፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥቃቶችና ጥሰቶች ቆመው ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለማቆም ድርድር እንዲካሄድ መስማማታቸውን አመልክቷል፡፡

መግለጫው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንትም እና በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ለሚያደርጉት የሽምግልና ጥረት ጠንካራ ድጋፋቸውን የገለጹ መሆኑን አመልክቷል፡፡ 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ አንተኒ ብሊንክን፣ በሶማሊያ ብሄራዊና የፌዴራል አባል ክፍለ ግዛት መሪዎች የሚያደርጉት የምክር ቤትና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ በአስቸኳይ ማጠናቀቅ ያለባቸው መሆኑን ገልጸው፣ የውጤቱን ተዓማኒነት ከሚያሳጣ ህገወጥ ድርጊት ነፃ መሆኑን ማረጋገጥን አስፈላጊ መሆኑን በአጽንዎት ማስገንዘባቸው በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብሌን ከሥልጣን የማንሳቱን ሙከራ የምትቃወም መሆኑን አመልክተው፣ ሁሉም ወገኖች ሁኔታውን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና መግለጫዎችን እንዲቆጠቡ በማሳሰቡ ረገድ በስልክ ውይይቱ ላይ መስማማታቸውን መግለጫው አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply