ብሊንከን የደቡብ ምስራቅ እስያ ጉብኘታቸውን አቋረጡ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በደቡብ ምስራቅ እስያ የሚያደርጉትን ጉብኝት በዛሬው እለት ማቋረጣቸውን ተገለጠ፡፡ 

ብሊንከን ጉዞውን ያቋረጡት ከሷቸው ጋር አብረው ይጓዙ ከነበሩት የጋዜጠኞች ቡድን መካከል አንዱ ለኮቪድ19 የተጋለጡ በመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በኢንዶኔዥያና ማሌዥያ ያደረጉትን ጉብኘት አጠናቀው ነገ ሀሙስ ወደ ታይላንድ ለመጓዝ እቅድ ይዘው እንደነበሩም ተመልክቷል፡፡

ብሊንከን ደቡብ ምስራቅ እስያን መጎብኘት የያዙት የቻይና ተጽእኖ እየጨመረ ነው በተባለበት አካባቢ ያሉአገሮች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላቸውን ህብረት እንዲያጠናክሩ ለማድረግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ብሊንከን በጎዟቸው ወቅት እግረ መንገዳቸውን በሰጡት መግለጫ፣ የመፈንቅለ መንግሥት ካደረገ 10 ወር በሞላው የማይንማር ወታደራዊ መንግሥት ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ እምርጃ መውሰዱን አስፈላጊ ሆኖ አግኝታዋለች ማለታቸው ተመልክቷል፡፡ 

በማይንማር የሰብአዊ ቀውሱ የተባባሰ ሲሆን በርካታ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply