You are currently viewing ብልጽግና ወንጌል ከቤተመቅደስ እስከ ቤተመንግሥት –  ዶ/ር ደረጀ ከበደ

ብልጽግና ወንጌል ከቤተመቅደስ እስከ ቤተመንግሥት – ዶ/ር ደረጀ ከበደ

መንግሥታት በቀንደ መለክትና በአዋጅ ሊያግዱት ሲገባ ቸል በማለታቸው በአመታት መካከል አድጎና መንድጎ፣ ብዙሃኑን አራቁቶ፣ ጥቂቶችን ሚሊኒየርነት ማማ ላይ የሰቀለ አስተምሮ ምን እንደሆን የሚገምት ሰው አለ? ታመው የሚማቅቁን ተፈውሳችሁዋል፣ የደህዩትን ባለጠጋዎች ናችሁ፣ አንድ ብር ስጡና እግዚአብሄር 10 ብር አድርጎ ይሰጣችሁዋል የሚለውንስ የተወላገደ ትምህርት ታውቁት ይሆን??? አማኝ የሚታመመውና የሚደሀየው ጠንካራ እምነት ሲያጣ ነው፣ አለበለዛ ክርስትያኖች አይደሀዩም አይታመመሙም የሚለውን ትምህርትስ ደርሳችሁበት ይሆን? የእግዚአብሄርን በረከት በግል ስጋዊ ጥቅም፣ በብርና በምድራዊ ቁሳቁስ ብዛት ብቻ የሚገለጥ፣ በካፒታሊስት ዋና መዲናዋ በአሜሪካ ተወልዶ በአፍሪካ ያደገውን የነ “ወንጌል ተጡዋሪዎች፣ ስራ ጠላቱዎች” ትምህርትስ ለይታችሁ አውቃችሁት ይሆን??ትክክል ገምታችሁዋል። የብልፅግና ወንጌል ይሉታል። እኔ ግን “የብልፅግና ወንጀል” እለዋለሁ።
ስለብልፅግና ወንጌልና እስተምሮ በዚህ ጊዜ መፃፍ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ይህ የወንጀለኞች ዶክትሪን የፕሮቴስታንት ክርዝማቲክ አማኞችን በየአጥቢያ ቤተክርስትያኖቻቸው ከማራቆት አልፎ ዛሬ አገራችንን ለመምራት ቤተመንግስት የተኮፈሱ ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድንና ጥቂት ፔንጤቆስጤ የስራ አስፈፃሚዎቻቸውን፣ ይሀው አደገኛ ዶክትሪን፣ ተብትቦ እንደያዛቸው ግልፅ እየሆነ በመምጣቱ ህዝቡ ሃገራችን የገባችበትን አሌ የማይባል እጥፍ ድርብ ሰቆቃ እንዲረዳ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው። ስለመሪዎቻችን በተለይም ስለ ጠ/ሚኒስትሩ እንግዳ የሆነ፣ በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ የአመራር ክፍተት፣ ፍዘትና፣ ንዝህላልነት ላለፉት ሁለት አመት ከመንፈቅ ፀጉራችንን ስንነጭና ጥርሳችንን ስናፋጭ የቆየን በብዙ ሚሊዮን የምንቆጠር ዜጋዎች፣ መልስ ላጣንበት የአስተዳደር ውድቀታቸው፣ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን ይህንን የምናብ እምነት properity Gospel ተንትኖ መረዳትና ማስረዳት አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ እናውቃለን።
አያችሁ ብልፅግና ወንጌልን የሚያምን ወይም የሚከተል ሰው በሃዘን፣በደህነት፣በበሽታ፣በተፈጥሮአዊ መቅሰፍት ሰፈር መገኘት አይፈልግም። ያ ማለት፣ ምርት በአንበጣ ተወሮ ገበሬ ሲያለቅስ ብልፅግና ወንጌልን የሚከተል ሰው የተፈፀመው ውርጂብኝ እንዳልተፈፀመ፣ ቀና ቀናውን በማሰብና (Positive thinking) በእምነት (strong faith) ድልን በማወጅ አንበጣውም ይጠፋል፣ ምርቱም ይተርፋል ነው የሚለው። ጥቃቱም በህዝቡ አለማመን፣ ወይም ህዝቡ በእግዚአብሄር ላይ በደል ፈፅሞ ወይም እምነት ስለጎደለው የተፈጠረ የሰማይ ላይ ቅጣት ነው ብሎ ነው የሚያምነው። ስለዚህም አዘኔታ የለውም፣ ለተጎዳው ህዝብ መራራት አይችልም። ስለዚህ ነው መሪያችን እርጉዝ ሆድዋ ተዘንጥሎ ፅንሱ ሜዳ ላይ ሲጣል፣ ዝንብ የሞተ ያህል እንኩዋን ርህራሄ ያላሳዩት። ለጠ/ሚኒስትሩ ያ ድርጊት አልተፈፀመም ወይም በሰለባዋ እምነት ጉድለትና ሃጢአት የተነሳ የተፈፀመ ስለሆነ ለሳቸው ምንም ማለት አይደለም። በሰለባዋና በእግዚአብሄር መካከል ያለ ነገር ነው ብለው ስለሚያምኑ ህዝብ ያለቅሳል እሳቸው ያፉዋጩብናል።
ጁዌል ኦስቲን የተባለው በአሜሪካን አገር በጣም የታወቀ የብልፅግና ወንጌል ፓስተር በመፅሃፉ “Become a better you” ላይ ያለው አይነት ነው።
“Dwell only on positive, empowering thoughts toward
yourself, “You will see God’s blessings and favor in a
greater way.”
“ሃሳብህን በገንቢ ሃሳቦች ላይ ብቻ አድርግ ያን ጊዜ የእግዚአብሄር በረከትና
ሞገስ በህይወትህ በትልቅ መንገድ በሙላትህ ይገለፃል”
ብልፅግና ወንጌልን የሚከተሉ መሪዎች፣ የሌሎችን ችግር ማየት አይችሉም (No Empathy)፣ ችግር፣ በሽታና ደህነት ለእምነታቸው ተስማሚ የድል ትርክት ስለማይፈጥር፣ እያለ እንደሌለ መቁጠርና ጭንቅላታቸውን አሸዋ ውስጥ ቀብረው በምድር ላይ ያለውን እውነታ መካድ ይቀላቸዋል። እውነታው ግን አንታመምም ቢሉም ይታመማሉ፣ ሃዘንን ቢክዱም ሃዘን ይደርስባቸዋል፣ የተፈጥሮ አደጋን የለም ቢሉም የተፈጥሮ አደጋ ዙሪያቸውን ሲከሰት ያዩታል። ወይ አለበለዛ ዶ/ር አቢይ እንደሚያደርጉት ሃዘን በሰሜን ሲከሰት ወደ ደቡብ መፈርጠጥ፣ ፅንፈኞች ህዝብን ሲያርዱ ወደ ኢሳያስ አፈወርቂ ግዛት ማቅናት፣ በመተከል ከ 300 በላይ አማራዎችና አብረው የተገኙ አገዎችም በመንግስት በተደገፉ ፅንፈኞች ሲጨፈጨፉ ወደ ደቡብ ሄዶ ስለፓርክ ማውራት፣ ወሎ በአንበጣ ሲመታ እሳቸው በአሩሲ የለማ የእርሻ ማሳን መጎብኘት፣ Go kart እየነዱ፣ ኢላማ ተኩስ እየተለማመዱ መዝናናት፣ በጉራ ፈርዳ አማራዎች ሲታረዱ ስለሃዘኑና ጭፍጨፋው ላለማሰብና ላለመመስከር ዝምታን መምረጥ፣ በጠቅላላ አይንን ጨፍኖ አላየሁም ወይም አልሰማሁም ነበር ማለት ሊኖርባቸው ነው። ሌላስ? በጃልሜዳ ለብዙ አመታት በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናት ተተተክሎ የነበረን መስቀል በአስተዳደሩ ትእዛዝ ከነበረበት ተነቅሎ አልሰማሁም ነበር ብሎ መሸምጠጥ፣ የቡራዩ ማፈናቀልንም አልሰማምሁም ነበር ማለትን ሊጠይቅ ነው። አልያማ ከለይ የዘረዘርኩዋቸውና ሌሎችም ያልተጠቀሱ በርካታ አሰቃቂ ወንጀሎችና የተፈጥሮ አደጋዎች በምድራችን በተደጋጋሚ አይናችን እያየ መከሰታቸውን የሚክድ ፍጥረት ከብልፅግና ወንጌል አማኞች፣ሰባኪዎችና ከ አሮሙማ ፖሊቲክስ አመራሮቻችን በቀር ማን ይኖራል? በሃገሪቱዋ እንብርት ላይ አየተፈፀሙ ያሉትን ጉዶች አላየሁም ነበር አልሰማሁም ነበር በሚል ፌዘኛ መሪ 110 ሚሊዮን ህዝብ ሲመራ እንግዲህ ከዛ በላይ መቅሰፍትስ አለ እንዴ? ጠ/ሚኒስትሩ በዋናነት ኢትዮጵያን የኦሮሞ ምድር ለማድረግ ካላቸው አጀንዳ ጋር የብልፅግና ወንጌል እምነት ፅንሰሃሳብ በአስተዳደር ስርአታቸው ገብቶ ታላቁንና የበለፀገውን የኦሮሞ የምናብ ምድር በቅዠትና በሰመመን እያጣጣሙ ወደፊት መሄድን እንጅ ሃዘንን፣ ድህነትን፣ ሞትን፣ የማሰቢያ ጊዜውም ልቦናም የላቸውም። ስለዚህ ለቅሶ ቤት ከመሄድ ሰርግ ላይ ቢገኙ ይመርጣሉ።የጠ/ሚኒስትሩ ፀጥታን አለማስከበርና፣ የጥቃት ሰለባዎችን በጊዜውና በቦታው ተገኝቶ ችግራቸውን አለመጋራት፣ አለማፅናናት፣ አለመካስና ከሚመጡት ጥቃቶች አለመጠበቅ ምክንያት የብልፅግና ወንጌል እምነታቸው ብቻ ነው የሚል ካለ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ የቀበረ ሰጎን መሆን አለበት። እንዳውም ላስረግጥ የምፈልገው ነገር ከብልፅግናውም ቅዠት ይልቅ የኦሮሙማ አጀንዳቸው፣ አማራን፣ አማርኛንና ኦርቶዶክስን የማጥፋት እቅዳቸው እጅግ የከፋና እንደሆነ ነው።
አንትያ በትለር (Anthea Butler) የተባሉ የስነመለኮት ፕሮፈሰር ስለፕሮስፔሪቲ ጎስፕል መሪዎች ሲናገሩ “ዶናልድ ትራምፕንና ጆዌል ኦስቲንን ያመሳስሉዋቸዋል። እንደ ፕሮፌሰሩዋ አባባል ሁለቱም ከአማኞች ትልቅ ቅቡልነት ያላቸው ናቸው፣ በስኬታማነትም ያምናሉ፣ ነገርግ ግን በወንጌል ቃል ላይ የተመሰረቱ ወይም የበሰሉ አይደሉም” ይላሉ። ሁለቱም ማለትም ዶናልድ ትራምፕና ጆዌል ኦስቲን እንደማንኛውም የብልፅግና ወንጌል ተከታይ፣ የአሸናፊነትን እንጅ የውድቀትንና የተሸናፊነትን ወሬ መስማት አይፈልጉም። ፕሮፌስሩዋ የበለጠ ግልፅ በሆነ መንገድ ሲያስቀምጡት ታዲያ፣ ትራምፕንና ኦስቲንን የመሰሉ የብልፅግና ወንጌል መሪዎች የጎርፍና የአውሎ ነፋስ ዜናዎች አይስማሙዋቸውም ምክንያቱም ከብልፅግና ወንጌል ዶክትሪናቸው ጋር የሚስማማ የድልና የፈንጠዝያ ወሬ ስለማያበስር። በዚያም ላይ የብልፅግና ወንጌል መሪዎች አደጋንና ክፉ ክስተቶችን አደብስብሶና አቃሎ የማቅረብ፣ ሰለባዎች የደረሰባቸውን አደጋና አካላዊ ጉዳት ደግሞ ከግንዛቤ ያለማስገባትና ከጉዳይ ያለመፃፍ ባህሪይ አላቸው ይላሉ። ደግ ደጉን፣ አሸናፊነትን፣ መበልፀግን፣ አዎንታዊ ስነልቦናን (እምነትን) ይዞ ለቅሶና ዋይታ የሌለባትን አሮምያን መገባት።
ልብ ብላችሁዋል? የኛም ጠ/ሚኒስትር አንትያ በትለር (Anthea Butler) የገለፀችው የጆዌል ኦስቲንና የዶናልድ ትራምፕን ጠባይና ተግባርን ኮፒ ነው ሲያሳዩን የኖሩት። የማፅናናት ቃል ከአፋቸው እኮ አይወጣም። በወሎው አንበጣ ወረራ ሰአት እሳቸው Go-kart እየነዱ ኢላማ ተኩስ ጨዋታ እየተጫወቱ ልክ እንደነ ኦባማና እንደ ሌሎች የሰለጠኑና ሃብታም አገር መሪዎች ለመሆን፣ ነገረ አለሙን ረስተው ይቡዋርቁ ነበር። በጣም የሚገርም አይነት መደንዘዝ ይላሉ ያ ነው እንግዲህ። እነኦባማ ቢጫወቱ ያምርባቸዋል። ኦባማ በኤኮኖሚ የተንኮታኮተች አሜሪካንን ከቡሽ ተረክቦ ሌት ከቀን ሰርቶ ሃገሪቱን ከሪሰሽን (Recession) ያወጣ ጀግና መሪ ነው። ቢጫወትም ያምርበታል። የኛ መሪ የተረከቡትን ሃገር ጥለው አንዴ ዱባይ ሌላ ጊዜ ደግሞ ኤርትራ የሚዞሩ፣ አገር መምራት አይደለም አንድ ሱቅ ማስተዳደር የማያውቁ፣ ለካሜራና ለታይታ የሚንቀሳቀሱ፣ በብሄር ተበጣጥቃ የአንድ ብሄር የበላይነት በፈረቃ የሚለዋወጥባትን አገር ለፅንፈኞች አሳልፈው ሰጥተው አገር ሲታመስ እንዳልሰሙና እንዳላዩ የሚሆኑ መሪ ናቸው።
ብልፅግና ወንጌል በቤተክርስትያን
የብልፅግና ወንጌልን አሰራር በቅጡ ለተመለከተ ሰው፣ በውስጡ ያዘለው ትምህርት ህዝብን በባዶ ተስፋና በወሬ፣ ያለውን እምነትና ንብረት የሚያስጥል፣ የመሰሪዎች “ በጨ ጠቆረ” ቁማር እንደሆን በቀላሉ ይረዳል። እንዲያውም የወንጌል አገልግሎት ሳይሆን አይን ያወጣ ዝርፊያ ነው ቢባል ማጋነን እይሆንም። ህዝቡ ያለውን ይሰጣል፣ ወትዋቹ ሰባኪ ግን የብር ፍቅር አስክሮት ጨምሩ በረከቱ በሰጣችሁት መጠን እንዲጨመርላችሁ ይላል። ብልፅግና ሰባኪው መድረክ ላይ ወጥቶ ህዝቡን ሲደልልና ሲሸጥ የጨረታ ገበያ አይነት ልፍለፋ መለፍለፍ አለበት። የምእመናኑን ልብ ለማባባት፣ ዝሩና አስር እጥፍ ታጭዳላችሁ ይላቸዋል። በኢየሱስ ስም የተለበጠ ወንጀል። በእስር ሊያስቀጣ የሚገባ ወንጀል። በካፒታሊዝም ስርአት የተለመደው፣ ግለሰቦችን በብዙሃን ላይ በገንዘብና በስልጣን የመቆለል ልምምድ (Individual achivement) የብልፅግና ወንጌል መሰረቱ ነው። ምን ማለቴ ነው? ብልፅግና ወንጌልን በመስበክ ሃብት ያካበቱ እንደነ ክራፍሎ ዶላር፣ እንደ ቲዲ ጄክ፣ እንደነ ኬኔት ኮፕላንድና እንደነጆይስ ማየር አይነቶች በአባሎቻቸው ላይ ያላቸው ተፅእኖ የአሽከርና የጌታ ያህል ነው። የእነኝህ ብልፅግናውያን አገልግሎትና እንቅስቃሴ ዋና የደም ስር የሆነው አባላቸው ደህይቶ፣ እነሱ ስመጥር ባለፀጋዎች ሆነዋል። በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ የሚንደላቀቁበትን ሃብት የሚሰጣቸውን ህዝባቸውን ራሱን መልሰው ሲንቁትና እንደ ጀሌያቸው ሲቆሩጡት ነው።
የብልፅግና ወንጌል አስተማሪዎች ምእመናኑን በእምነት ከጌታ በረከትን እንዲጠብቅ ያስተምሩታል እነሱ ግን “እጅ በእጅ ፍቅር እንዲደረጅ” እንዳለው የሃገሬ ጉራጌ፣ በእምነት ሳይሆን በሚታይና በሚጨበጥ ጥሬ ገንዘብ (cash) ነው የሚደራደሩት። የአባሎቻቸው አስራትና ስጦታ ለሽቶ፣ ለሱፍ፣ ለጫማ፣ ለውድ መኪናዎች፣ ለግል ፕሌኖች፣ ለወርቅ፣ ለብዙ ሚሊዮን ዶላር ቤቶችና ለወፍራም የግል ባንክ አካውንት ነው የሚውለው።
ስለብልፅግና ወንጌል ማንበብ የጀመርኩት ከብዙ አመታት በፊት ነበር። ከ 20 አመታት በፊት አሜሪካ በብልፅጋና ወንጌል ቴሌቪዢን ሰባኪዎች (Televisionpreachers/Teleevangelists) ቁማርና ወንጀል ታምሳ በነበረበት ጊዜ እኔ እዚሁ አሜሪካ አሁን የምኖርበት ስቴት ነበር የምኖረው። እውቅና የነበራቸው የብልፅግና ወንጌል አስተማሪዎች አንድ በአንድ ወደላይ እንደወጡ እንደ ሉሲፈር ወደታች የተወረወሩባቸውን ወቅቶች በደንብ አስታውሳለሁ። ከፀጋ ከወደቁት የዶክትሪኑ አስተማሪዎች አንዱ የሆነው ጂም ቤከር የምእመናንን ገንዘብ ወደግል አካውንት በማዘዋወር ተከሶ ከሚወዳት ሚስቱ ከታሚ ቤከር (ወደ ጌታ ሄዳለች ከብዙ አመታት በፊት) ተለይቶ በ48 አመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበት ወደ እስርቤት ሲላክ ቴሌቪዥን ላይ ተጣብቆ የተከታተለው የአሜሪካ ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም። በሁዋላ ግን የጂም ቤከር ቅጣት በጥሩ ጠባይ ተቀንሶለት ከ 8 አመታት በሁዋላ ተፈታ። ያ ዘመን የብልፅግና ወንጌል ቴሌቪዥን ሰባኪዎች ዙሪያ ገፃቸውን በህዝብ ቁጣ ተከበው የነበረበት ዘመን ነበር። ሌላው ትልቅ የመነጋገሪያ ርእስ የነበረው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ ኦራል ሮበርት በ 1987 በህዝብ ፊት፣ በህዝብ መገናኛ ወጥቶ “እግዚአብሄር በአንድ ወር ውስጥ 8 ሚሊዮን ዶላር ካልሰበሰብክ እገድልሃለሁ ብሎኛልና እባካችሁ ገንዘብ ስጡኝና ከሞት አድኑኝ” ብሎ ተናገረ። መቼም የአሜሪካን ህዝብ የዋህም ሩህሩህም ነውና የተባለውን ገንዘብ በተባለው ጊዘ ሰበሰበለት። የሚገርመው ግን ያም በቂ አይደለም ብሎ ሌላ 8 ሚሊዮን ብር እንዲሰበስቡለት የጠየቀበት ሁኔታ ነበር ያለው። እግዚአብሄር ብር ካላዋጣህ እገድልሃለሁ ብሎኛል ማለቱ በማያምኑ መካከል ሳይቀር መሳለቂያ ነገር ሆኖ ነበር። ከዛም ወዲህ በተለያዩ ወቅቶች የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች እንደነ ቢሾፕ ላንግ (ነፍስ ይማር)፣ ሮበርት ቲልተን፣ ጆዌል ኦስተን፣ ቲዲ ጄክ፣ በኒሂን፣ ክራፍሎ ዶላር፣ ጆይስ ሜየርና ሌሎችም በርካታ ብልፅግናውያን የአገልግታቸውና የእለት እለት እስረሽ ምቺው ህይወታቸው ጉዳይ ለትልቅ ምርመራ (Scrutiny) ተዳርጎ ነበር።
መቼም ምን አለፋችሁ በወንጌል ታሪክ ውስጥ በጴንጤቆስጤና በሌሎችም ክርዝማቲክ ቤተክርስትያናት ውስጥ በተለያየ ወቅት ከተነሱት ሃሰተኛ ትምህርቶች ሁሉ አንደ ብልፅግና ወንጌል (prosperity Gospel) አማኙን ህዝብ ከምድር ዳርቻ እስከምድር ዳርቻ የጎዳ ትምህርት የለም። ዛሬም እየተራባ ነው። ብልፅግና ወንጌል የማያሻማ ስርቆት ነው። ስለዚህም ይህ የአጭበርባሪዎች ትምህርት በብዙ መንገድ ቤተክርስትያናት ብቻ ሳይሆኑ መንግስትም ሊከታተለው የሚገባ ነገር ሆኖ ሳለ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከልካይ ስላላገኘ ከአመት ወደ አመት እየሰፋና እያደገ ነው የሄደው። እውነትን ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን አገልጋዮችም ጭምር ይህንን ትምህርት በሃገራችን ህዝብ መሃከል የሚዘሩ አጭበርባሪ ሰባኪዎችን ሁሉ በአንድነት እንዲያወግዙም ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ብልፅግና ወንጌል ከየት መጣ እነማን አመጡት?
የብልፅግና ወንጌል ፅንሰሃሳብ የተፈጤረው የእምነት ቃል (Word of faith) ከተባለ ትምህርት ነው። የእምነት ቃል በጭሩ አንድ አማኝ ቀና ቀናውን በማሰብና በእምነት ከፈጣሪ እንዲደረግለት የሚፈልገውን ነገር በንግግር/በአንደበቱ በመናዘዝ/በመናገር በአእምሮውም ሳይጠራጠር በመቀበል የልቡን መሻት ሊያገኝ ይችላል ብሎ የሚያስተጋባ ሀተታ ነው። ይህ ዱቄት እንኩዋን መያዝ የማይችል ወንፊት ትምህርት/እምነት በአጋጣሚ ከሚሊዮን እንድ ካልሆነ በተቀር የማይፈፀም የቅዠት ነፀብራቅ ነው። የእምነት ቃል (word of faith) በ 20 ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ በክርስማቲክ ጴንጤቆስጤዎች ጎራ የተፈጠረ ትምህርት ሲሆን ትምህርቱ እግሮች አውጥቶ እንዲሮጥ ያደረጉት ወስላታ የእምነት አስተማሪዎችና መሪዎች አሉት። ከነዚያም ውስጥ ኬኔት ሄገን የተባለው ሰው የትምህርቱ አባት በሚባል ይታወቃል። ነገር ግን ከእሱ በፊት የቃለ እምነትን መሰረት የጣለው ፋይነስ ፓርከርስት ኩዋምቢ (Phineas Parkhurst Quimby (1802-1866) የተባለ ሲሆን ፋይነስ ለኬንዮን፣ ኬንዮን ለኬነት ሄገን እንዳስተላለፉት ነው የሚታወቀው። የእምነት ቃል “የሰው እምነት እግዚአብሄርንም ያዘዋል ነው የሚለው። በዛም አባባል “”እምነት” ከእግዚአብሄር ውጭ የሚሰራ ራሱን የቻለ ሃይል ያስመስለዋል። እውነታው ግን ሰው እምነትም ኖሮት የጠየቀውን ወይም የፈለገውን ከእግዚአብሄር ላያገኝ ይችላል። ወይም “የፈልጉትን ሰጣቸው ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ” (መዝሙር 106: 15) እንደሚል አንዳንዴ የፀለይንበትን አግኝተን ነገር ግን ጥቅሙ ሳይሆን ጉዳቱን እናጭዳለን። የ ”ቃለ እምነት” ወይም “የእምነት ቃል” አስተማሪዎች በቃሉ ላይ ከመመስረት ይልቅ እግዚአብሄር በተለየ መንገድ ለእነሱ የሚገልጠው የተለየ የቃለ እምነት መገለጥ አለ እያሉ ነው ህዝብን የሚያጭበረብሩት። መፀሃፍ ቅዱስን የእነሱን አጀንዳ እንዲደግፍ እድርገው በመተርጎም ያው እንደሚታየው በህንፃ ላይ ህንፃ የሚገነቡ ቢሊዮነሮች ሆነው ቁጭ ብለዋል። መፀሃፍ ቅዱስን ቁጭ አድርገው በመገለጥ፣ አየን ወይም ሰማን በሚሉት መሰረት ዬለሽ ቅብጥርጥር ሰውን ይዋሹታል፣ይዘርፉታል፣ ያደሀዩታል፣ ያሞኙታል።
የቃለ እምነት (Word of faith) በጨረፍታ
1/ሰዎች ትናንሽ እግዚአብሄሮች ናቸው ምክንያቱም ሲፈጥሩ ሙሉ የእግዚአብሄርን ባህሪይ ተሰጥቶአቸዋል ይላል። ሰው በምድርንና በውስጡዋ ባሉት ላይ ትንሹ እግዚአብሄር እንዲሆን እንዲያዝና እንዲገዛ፣ እግዚአብሄር ስልጣኑንና ሃይሉን ሰጠው። እግዚአብሄርን የሰማዩን መንግስት ሲመራ ሰው ደግሞ ምድሪቱን ሊገዛ
ማለት ነው (Capps, Authority in Three Worlds, pp. 16-17).
እውነታው ግን በሰማይም በምድርም አንድ እግዞአብሄር ብቻ ነው ያለው። ሰው መቼም እግዚአብሄር አልነበረም አይሆንምም (ዮሃንስ 17:3)። ከሱ በፊት ከሱ በሁዋላም ሌላ እግዚአብሄር አልተፈጠረም እይፈጠርምም (ኢሳያስ 43 : 10).
2/ እምነት በቃል የሚንቀሳቀስ ሃይል ነው። የሚጨበጥ የሚዳሰስ ያህል ነገራትን የሚያንቀሳቅስ፣ እግዚአብሄርን የሚያዝ ግፊ ነው።
እውነታው ግን እምነት በእግዚአብሄር ቃልኪዳኖች ላይ መታመን ብቻ ነው። (እብራይስጥ 11:1)። እምነት ብቻውን እግዚእብሄርን አያዘውም። እኛ የሰው ልጆች የማናውቃቸው ነገርግን እግዚአብሄር የሚያያቸው፣ የሚያገናዝባቸው ነገሮች ሁሉ ለጠየቅነው ነገር ከእግዚአብሄር ምን አይነት መልስ እንደምናገኝ፣ መቼ እንደምናገኝ ይወስናሉ። እምነት አለኝ ገንዘብ አምጣ የምንለው አምላክ አይደለም የምናመልከው።
ብልፅግና ወንጌል ከቃለ እምነት ጋር የተያያዘ ሆኖ ሳለ አንድ ልዩነት ግን አላቸው። ያም ልዩነት የብልፅግና ወንጌል ወሮበላዎች በእምነት ውስጥ ገንዘብን አስተዋወቁ።ለመጀመሪያ ጊዜ “የእምነትን ቅንጣት ዝሩ” ማለት የጀመረው ከላይ የጠቀስነው ኦራል ሮበርት የተባለው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ ነበር። አያችሁ የእምነትን ቅንጣት የምትዘሩት በገንዘብ ነው ማለት ነው። አማኞች ለምን የእምነትን ቅንጣት በእምነት፣ ገንዘብና ወርቅ በሌለበት መዝራት አይችሉም?? ያቺ ለእምነት ቅንጣት የተጠየቀችው ገንዘብ ወደሰባኪዎቹ ኪስ የምትገባ ገንዘብ ናት። ያቺ ገንዘብ ቀላል ገንዘብ አይደለችም። ብዙዎቹን የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች የግል ጄት ባለቤቶች እንዲሆኑ ያደረገች ያቺ የእምነት ቅንጣት (seed of faith)ብር ናት። በአሜሪካን አገር በ”እምነት ቅንጣት” ዝሩ ሳቢያ የናጠጡ የወንጌል ወስላቶች በአሜሪካን አገር በአንድ ወቅት በኮንግረስ ሳይቀር ገቢና ወጪያቸው እንዲመረመር ተደርጎ ነበር።
ብልፅግና ወንጌል ከሌሎች ሃሰተኛ ትምህርቶች ሁሉ የከፋ ነው ብዬ ያልኩበት ምክንያት ምንድነው?
የብልፅግና ወንጌል
1ኛ/ የእግዚአብሄርን መለዮና ባህሪይ ደልዞ የሌለውን ባህሪይ የሰጠዋል። እግዚአብሄርንና ምድራዊ ሃብትን ያዛምዳቸዋል። እግዚአብሄርና ገንዘብ ምን ያገናናቸዋል? ገንዘብ ለሰጡት ገንዘብ የሚሰጥ ላልሰጡት ደግሞ የማይሰጥ? ገንዘብ ከሰጡት ጤንነትንና ስኬትን የሚሰጥ፣ ገንዘብ ካልሰጡት ግን ግድ የሌለው? ለመሆኑ ይህ የእግዚኣብሄር ባህሪይ ነው? አይደለም (ማቴዎስ 19:23-24 ፣ 1 ጢሞቲዎስ 6:10)
2ኛ/ የእምነትን ምንነት፣ በአማኞች ህይወት ውስጥ የሚጫወተውንም ሚና ፍፁም ያጣምመዋል።
የእምነት ቅንጣት (ዘር) ና ገንዘብ ምን አገናኘው? እምነት የእግዚኣብሄር ስጦታ ነው። እምነት ሰው ከእግዚኣብሄር ጋር የሚዋሃድበት መለኮታዊ ልምምድ ነው። በገንዘብ አይገኝም። በገንዘብ አይሸጥም፣ በገንዘብ አይለወጥም (ኤፌሶን 2:8)
3ኛ/ በደህነት የሚማቅቁንና በበሽታ የጎሰቆሎ ሰዎችን ኢላማ ያደርጋል።
ስለዚህም በአሁኑ ወቅት የብልፅግና ወንጌል ዋና መራቢያ ቦታ አፍሪካ ሆኖአል።በኢትዮጵያም በግልፅ ይህንን የሌብነት ወንጌል እየሰበኩ ህዝቡን የሚሰርቁ ሰባኪዎች አሉ። እነሱን በህብረት ማውገዝ ይገባል። ያላችሁን ሙዋጣችሁ ከሰጣችሁ ሃብታም ትሆናላችሁ፣ ጤና ትሆናላችሁ ፣ በሚል የቀረቻቸውን ቤሳና በእግዚኣብሄርም ላይ ያላቸውን እምነት ይነጥቃቸዋል።
4ኛ/ ብልፅግና ወንጌል የሚያበለፅገው ሰባኪውን ወይም መጋቢውንና የእርሱ ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች የሆኑትን ኣጃቢዎቹን ብቻ ነው።
ህዝቡ ግን ያለውን ለመጋቢው ወይም ለሰባኪው ሰጥቶ ላም አለኝ በሰማይ እናዳለ በባዶ ተስፋ አይኑን እንዳፈጠጠ ይቀራል።
5ኛ/ ህዝቡ ያለውን እየሙዋጠጠ ከሰጠ በሁዋላ በሰባኪው የተነገረው የሰማይ ብርና ወርቅ ሲዘገይና ሳይከሰት ሲቀር፣ ጮሌው ሰባኪ መልሶ እምነት ስለጎደለህ ነው፣ ሃጢትህን ስላልተናዘዝክ ነው ከእግዚኣብሄር ገንዘብ ወይም ጤንነት ያላገኘሀው ወይም ያላገኘሽው ብሎ ጥፋቱን በተዘረፈው (ችዋ) ደሃ ይላክካል።
ይህም አሰራር ዋሾው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ (ዘራፊ) የእኔ ጥፋት አይደለም ብሎ እንዲያሳብብ ቀዳዳ ከመስጠቱም በላይ ተዘራፊዎቹ የደረሰባቸውን ጥቃት በራሳችን ጥፋት ነው ብለው እንዲቀበሉና ወደ ህግም እንዳይሄዱ ያግዳቸዋል። የጥቃት ጥቃት።
6ኛ/ እግዚአብሄርን በፎርሙላ ማንቀሳቀስ ይቻላል ይላል። ልክ እንደ ሂሳብ ትምህርት የተደነገጉ የአሰራር ፎርሙላዎችን ለተከተለ ሁልጊዜ ወደተጠበቀው ውጤት እንደሚወስድ ሁሉ የብልፅግና ወንጌል ትምህርትም አንድ ሰው እምነት ካለውና ይሆንልኛል ብሎ እስካመነና በቃሉም እስከተናዘዘ ድረስ ወይም በአእምሮው የጠየቀውን ነገር ሲቀበል ማየት ከቻለ የጠየቀው ነገር ከእግዚአብሄር የሰጠዋል ይላል። ይህ ደግሞ ፍፁም ውሸት ነው። የእግዚአብሄር ምላሽ አወንታ ወይም አሉታ የሚሆንበት ምክንያት ሁልጊዜ ለሰዎች አይታወቅም። እግዚአብሄር ስራው በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ናቸው። እምነትም ኖሮን፣ በቃላችንና በስነልቦናችንም ተናዘን የጠየቅነው ነገር ላይሰጠን ይችላል። ወይም ገንዘብ ጠይቀን ጤንነት እንቀበል ይሆናል። እግዚአብሄር በፎርሙላ አይሰራም። ማንም አያዘውም።
አገራችን
የአገራችንን ምስኪን ህዝብ የሚግጡ የብልፅግናና የቃል እምነት (word of faith) ሰባኪዎች ደሃውን ህዝብ ሃብታም ትሆናለህ፣ ከበሽታህ በእምነት ትፈወሳለህ፣ ደህነት አይነካህም ከእንግዲህ እያሉ በጋጡት ገንዘብ ሚሊየነሮች ሆነዋል። እንዳንዶቹ ከየክልሉ ሌሎቹም ከዛው ከአዲስ አበባ የተጠራቀሙ የኢየሱስን ስም የሚሸቅጡ ነውረኞችና ዘራፊዎች ከፍተኛ ድጋፍ ከዚህ ከወንበዴ መንግስት ስላገኙ ያለምንም ፍራቻ ወንጀላቸውን እየፈፀሙ ነው።ዶ/ር አቢይ አህመድ የወንጀለኞች ሹዋሚ ጠ/ሚኒስትር ቤተመንግስታቸው ድረስ ከሚጋብዙዋቸው ውስጥ የቃል እምነቶችና የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ አጭበርባሪዎች ይገኙበታል። እንዲያውም እነኝህ ዘራፊዎችና ጤናማ ወንጌል ሰባኪዎች ይቅር ተባብለው አንድ ማህበር እንዲጠጡ ባዘዙት መሰረት ከጥቂቶች በተቀር ካውንስል መስርተው በአንድ ተቁዋዳሽ ሆነዋል። ጤነኛዎቹ ተብለው ይከበሩ የነበሩ ሰባኪዎችና መጋቢዎች፣ ሃሰተኛ ነቢያትንና ሃዋሪያትን (እነሱው ናቸው ብልፅግናና ቃል እምነትን የሚሰብኩት) አቅፈው ስመው “ድሮም እኮ ልዩነታችን ጥቃቅን ነበር” “ስራቸውን እንጅ እነሱን አልጠላም” የሚሉ ሰበቦችን እያዥጎደጎዱ በአንድ ላይ “በካውንስሉ” ስም ይሰራሉ። ጤናማ ዘማሪዎችና ሰባኪዎችም በካውንስሉ ስብሰባዎች እየተገኙ ፕሮግራማቸውን ያደምቁላቸዋ። ዛሬ “ሰው ትንሹ እግዚአብሄር ነው” የሚሉ ወሮበላዎች እድሜ ለጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ ወደ ከርቸሌ መጋዝ ሲኖርባቸው ምላሳቸውን እያወጡ ያላግጡብናል። ባለዲዛይነር ሱፎች ናቸው። ከየት አመጡት ገንዘቡን አይሰሩ አይነግዱ? ከምስኪን ደሃዎች፣ ከህመምተኞች፣ እምነተ ለጋዎች ኪስ ነው የሰበሰቡት።
መንግስቱም ወስላታ
መሪውም የማይታመን
ሰባኪውም ኪስ አውላቂ የሆነባት አገር እግዚኦ !!!!!!!!!!!!!!
ይህ ሴይጣናዊ ትምህርት በአሜርካም ሆነ በአፍሪካ እንደ ሰደድ እሳት የተሰራጨው በኢኮኖሚ በተጎዱት ህብረተሰቦች መካከል ነው። ምክንያቱም ግልፅ ነው። ደሃ ከደህነቱ የሚያላቅቀው ነገር አለ ከተባለ የትም ይሄዳል። ምንም ያድርግ ?። ህዝብ ሞኝ ስለሆነ ሳይሆን ቢጨንቀው ነው ብልፅግና ብልፅግና የሚሉትን ሰባኪዎች የሚከተለው። የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች አፍሪካ ድረስ ዘልቀው ታዋቂ መጋቢዎችን እየተጠቀሙ በቀን ከአንድ ዶላር በታች ከሚያገኘው ህዝብ ሳንቲም ይቃረጣሉ። የዚህ ስህተተኛ ትምህርት አዛማቾች በቀጣዩ አለም በእግዚኣብሄር ዘንድ የሚጠየቁ ቢሆንም በምድር ደግሞ ብዙ ጥፋት ሳያጠፉ በፍርድቤትና በዳኞች ፊት ሊቀርቡ የሚገባው ነው። እውነትን የሚወድ ሁሉ ደግሞ ሊያወግዛቸው ይገባል።

This Post Has 4 Comments

  1. Genet Mekdes

    Dear Dr. Derje Kebede
    Thank you for this article, which I find relates a legitimate concern about the Prosperity Gospel spreading out in Ethiopia now, that you seem convinced to be nothing more than a tool to fool and rob the poor and gullible not to mention the greedy but quite IGNORANT population.
    Before I came across your post and read it I had no idea this gospel and other similar related teachings have not only reached our Nation but according to your assessment are actually taking root there.
    Since I am always interested to know about spiritual practices and philosophies that are being preached and/or being practiced by humans across the globe I thank you for enlightening me about what is going on in the Ethiopian Charismatic Pentecostal Churches regarding this seemingly ‘newer’ teachings/s which, as you also mentioned includes this teaching which I believe you find very OFFENSIVE:
    “ሰው ትንሹ እግዚአብሄር ነው”
    That said, with all due respect and you don’t necessarily have to agree with me but I would like to try to briefly and in summery form share with what I know about both topics.
    First I would have you know if you are willing to look and research a bit deeper into both of these teachings I have no doubt that you will come to discover that both of these teachings are actually based on sound and true Spiritual Principles/Truism having their base not only in our Christian Scriptures but also in all the scriptures of the great religions of our world.
    The reason that you understandably are upset and could only see it only as a ‘threat’ to the public no doubt stems from the way the True Message has been Distorted by the charlatans who hijacked it’s true meaning and specific application not to mention the the requirements to be fulfilled for any of these things to really WORK.
    For instance regarding the use of Power of Faith and Speech/Affirmation and Conviction for humans to materialize desired result much scripture support can be found in our Christian Bible.

    Just to mention a few examples of this may suffice here to make my point.
    In the Christian N.T. Bible the Spiritual Master Teacher Iyesus has revealed to us that Faith as small as Mustard Seed can and will move Mountains.
    He has also stated: ‘As a man THINKS So IS HE’.
    The Bible also teaches that “Death and Life is in the Power of the Tongue”.
    So these teachings overall are Biblically correct per many scriptures which give it support.
    In fact to simplify the whole objective of this so called ‘prosperity gospel’ we could term it as an attempt to practice a form of ‘Magic’.
    Let us not get alarmed about the word Magic, since it has many categories:
    White /black/active/ passive etc.
    Prayer itself for instance could be understood as a form of Magic in it’s own right.
    Anytime we humans try to alter a certain undesirable ‘reality’ to a more desirable state through prayer and by the use of our words and intention etc as in repeated Affirmation (prosperity gospel?) is basically an attempt to performing Magic.

    So what then really is the problem with this ‘Prosperity Gospel ‘ itself if it is just a form of Prayer so to speak, notwithstanding the way it is being presented to people with entanglement of the spiritual gospel with that of worldly treasures?
    If we could agree that this gospel falls under the topic of the Art of Magic,
    …well..like any worthwhile art one needs to cultivate the Discipline through rigorous proscribed Methods in order to acquire all the necessary Knowledge before one can venture out to practice it ‘successfully’.
    For instance in corroboration with the supporting Scriptures modern psychology’s’
    input regarding the human psyche has to be studied and understood.
    This is so in order to understand how it all Works ..if it is hoped to work.
    Looked from this angle for instance there are proven methods to be followed in order to successfully materialize or change a situation including for example ‘bad habits’ such as smoking or alcohol abuse etc.
    One method used for this is via transmitting a focused suggestion to impregnating our Subconscious Mind with our words, deep convictions and thought using our Will and Desire Nature.
    Hypnosis is a similar practice as well which addresses the Subconscious to birth forth the outcome per the suggestion it receives from the Conscious mind.
    All these methods may sound easy to do or follow, but I assure you they are NOT and therein may lie the ‘Charlatans chance to dissemble and use it for their own selfish purposes.
    I venture to state, at the least those so called expert teachers of this ‘get rich with your wish’ scheme’ know that Our Subconscious Mind is not easily reached (Sub=under)
    not to mention the fact that it is not easily ‘fooled’ either.

    This suggests these ‘preachers and teachers’ maybe well aware of this very important fact/factor but are still out to make a quick buck and that is as you’ve pointed out and I do fully agree, quite deplorable and needs to be denounced.

    But for those people who may wish to investigate deeper about the whole matter, I believe, it may be a huge blessing that may help them to open up a path to understand themselves more.

    Which brings me to the next topic you mention in your post:
    “ሰው ትንሹ እግዚአብሄር ነው”
    So.. Is man a little god?
    The answer to this question is a huge unequivocal Yes and at the same time an equally firm Huge NO.
    How is that possible you may ask?
    Well…it all depends on the Level of Consciousness we are referring to here when we speak of man ‘as little god’ or when we speak of him ‘as little ‘devil’.

    To understand what I mean by this, the first thing we need to know about is our so called Human Nature. When we speak of Human Nature we need to identify which one of his Natures we are referring to.
    Our Human Nature is complex, but simply putStill evolving.
    So we can easily see the very contradictory nature of this whole ‘prosperity gospel’ which more than anything caters to the Ego/ Lower Nature of Man.
    For.. a highly developed Consciousness has not much desire nor need for More and More of the World. Including MONEY.
    (‘ My Kingdom is NOT of this WORLD’ Jesus the Christ.)
    In conclusion then, it would be more correct and TRUE to state
    that > Man is a god in the making. And we have a long way to go.
    That being said, for Christians then.. our very Shining example of this long evolutionary process of the Soul to reach ‘godliness’ is none other than Jesus the Christ Himself.
    For Christians who are not afraid to ask and to seek to know the true teachings of the Christian Bible, they will come to understand and even ‘KNOW’ for themselves that the Bible is not just telling us a story about a man called Jesus.
    Rather the story of Jesus Christ in the Bible is our own story!!
    To quickly sum the story of Jesus In the Bible:
    Jesus the First Adam who the Bible states was ‘the first fruit among many bretheren’..was Anointed by God as CHRIST.
    At that point Jesus the first Adam becomes Jesus the Christ.
    Thus , that is why the Bible calls him:
    The Second ADAM.
    In conclusion then about both topics,.. I agree with the Bible when it points out the Prerequisites for Spiritual Development is indispensable:
    ‘MY people perish from Lack of KNOWLEDGE’.
    Blessings to you my brother!
    Blessings to All my brothers and sisters in Ethiopia and Beyond. Amen!

  2. Tesfa

    ሃይማኖት የመኖሪያ ብልሃት ሆኖ ለዘንተ ዓለም ሰውን ሲግጥ ኖሯል። የዛሬውን ከበፊቱ የሚለየው ነገር ቢኖር የምዕመናኑ ኑሮና ህይወት ሳይለወጥ መድረክ ላይ ቆመው አምሮባችሁሃል፤ ድናቹሃል፤ ትልቅ ቤት ታገኛላችሁ፤ ስጡ ይሰጣቹሃል ወዘተ በማለት የሚያደናቁሩት የሰዎች ቁጥር መብዛቱ ነው። እነዚህ ስመ አገልጋዪች የሚታወቁት በሚነድት መኪና፤ ዘርፈውና አዘርፈው በሰሩት ቤት እንጂ በአገልግሎቻቸው አይደለም። የሚያሳዝነው የሚነገረውን ሁሉ ሳያኝክ የሚሰለቅጠው ሰው እንደ አሸን መፍላቱ ነው። የብልጽግና ወንጌል አንድ የማታለያ መንገድ ነው። ዛሬ በናይጄሪያ፤ በደቡብ አፍሪቃ፤ በጋና፤ በኢትዮጵያ በፈጣሪ ስም ሰው እሳርና ቅጠል እንዲበላ የሚያረጉ፤ ትጥቅ ባነገቡ ጠባቂዎች የሚታጀቡ፤ ያልኖሩበትንና የማያውቁትን የተጸለየበት የጨርቅ እራፊ፤ መጽሃፍት፤ ዘይት ወዘተ… እንደ ሃገራችን የጉልት ሽያጭ የሚቸረችሩ በቃኝን የማያውቁ ተኩላዎች የሚራወጡባት ምድር ላይ እንኖራለን። ሃይማኖት መሸንገያ እንጂ እውነትነት የለውም። እውቁ የነጻነት ታጋይ ጆሞ ኬኒያታ እንዳሉት ” እንጸልይ ብለውን አይናችን ጨፍነን ስንጸልይ ሲከፈት መሬታችን ተወስዶ አየን” እንዳሉት ነው።
    ለመሆኑ ሃይማኖት ወይም እምነት ምንድን ነው? ሰው ለአመነበት ነገር ቆሞ የሌላውን መልካምነት ልክ እንደራሱ የሚያይበት ዘይቤ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው ትንታኔ ሁሉ ለወፎች የሚሰጥ ዘር ነው። ታዲያ በዚህ መስፈርት ሰው አንገቱ ሲቀላ፤ ቤት ተዘግቶበት በእሳት ሲጋይ፤ ልጅና ሚስት ኡ ኡ እያሉ ባል በጩቤ ተቆራርጦ ሲገደል ዝም የሚል ቤ/ክርስቲያን ኦና እንጂ ሰው ያለበት አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ አማኝ ነው ይሉናል። ውሸት ነው። ይህን ተግባሩ ያሳያል። ማታለል፤ ማጭበርበር፤ መግደል፤ ማስገደል፤ ምቀኝነትና ሽኩቻ የበዛበት ይህ ህዝብ ፈጣሪን ያውቃል የሚሉ ሁሉ ሆዳቸው የሞላ መጠለያ የቆመላቸው በምድሪቱ የሚያነቡ አይኖችን ማየት ያልፈቀድ ከርሳሞች ብቻ ናቸው። የሰው ልጅ መኖር የሚለካው ለሌላው በመኖሩ ነው። እልፍ መስጊዶችና ቤተ ክርስቲያኖች ( የኦርቶዶክስና የሌሎችም እምነት) ጭምር የተገተሩባት የሃበሻው ምድር ዛሬም እንዘጥ እንዘጥ ትላንትም ውጣ ግባ ወደፊትም ያዘው ጥለፈው ብቻ የሞላባት ምድር ናት። የንስሃ አባቱ፤ ወንጌል ሰባኪው፤ ፓስተር፤ ነብይና ነቢይት፤ አገልጋይ፤ ሸሁና ሌላውም ዘራፊና አታላይ ለመሆናቸው ከኑሮአቸውና ከስራቸው ማየት ይቻላል። ይህ ሲባል ለፈጣሪ ያደሩ፤ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ጥቂቶች ስለመኖራቸው ዓሊ ሊባል አይገባውም። አሉ ወደፊትም ይኖራሉ። ሰውም ራሱን ከቀን ወደ ቀን ለውጦ፤ ለእኔ ብቻ ማለቱ ቀርቶ የሌሎችንም ሰቆቃ ተጋርቶ ከኖረ ጥቂቱ ብዙ ነው። ያለዚያ ያው የሃብት መከመር ከሞት የታደገው ማንም አይኖርምና ሰብሳቢው ሳይሆን ሌላው ይበላዋል። አቶ ከበደ ሚካኤል – የቅኔ ውበት በሚለው መጽሃፋቸው ላይ እንዲህ ይሉናል።
    ይህን ያህል ዋጋ በሥነ ፍጥረቱ
    ትልቅ እንዳይመስልህ የሰው ልጅ በእውነቱ
    እየተሻሻለ ሁልጊዜ ታድሶ
    መፈጠር ይገባል ራሱን መልሶ
    እንዲህ ነው ህይወት። የማያቋርጥ ውሃ። አረንቋና ቁሬ ከመሆን የዳነ። አጠገቡ ላለው ብቻ ሳይሆን እንደ ወራጅ ውሃ በሄደበት ሁሉ ራሱን የሚያካፍል። የመኖር ሚስጢሩ ይህ ነው። በቁሳዊ እይታ የታወረው ይህ የአሁኑ ዓለም ፈጥኖ በመንቃት ከህዋላው የቀሩትን ዞር ብሎ ማየት እስካልቻለ ድረስ አወዳደቁ እንደ ሮም እንደሚሆን ከአሁኑ ግልጽ ነው።
    ሌላውን አስቆ ራሱም ያልሳቀ
    መኖሩን አያውቅም ካልተንከተከተ።
    እኮ በሉ ንገሩኝ እስቲ ወገኖቼ። አሁም ማን ይሙት የክልል ፓለቲካ ሃገር ያቆማል? የትግራይ እናት እንባ ከአማራዋ እናት እንባ ይለያል? መቼ ነው መገዳደላችን፤ መዘራረፋችን ቀርቶ በራሳችን አስበንና ቆመን ከነጭና ከአረብ ስነ ልቦናዊ ሰለባ የምንወጣው? ጠብቆ ማየት ነው። ከዛሬው ይብቃኝ!
    ዛሬ የዓለማችን ትልቁ ችግር እውነትን ከውሸት መለየት ነው። ሁሉ ዜና አቅራቢ፤ ሁሉ ማይክሮፎን ይዞ ለፍላፊ፤ ሁሉ በዚህም በዚያም አዋቂ ሆኖ በተሰለፈበት በዚህ አርቲፊሻል ትውልድ መካከል ስንዴን ከገለባ መለየት እጅግ አስቸጋሪ ሆኗል። ሁለት የዓለም ጦርነቶችን ያስተናገደችው ይህች አለም ዛሬም ቋፍ ላይ ሆና ሌላኛውን እየጠበቀች እንደሆነ የሚያሳዪ አመላካች ነገሮች አሉ። በተለይ በሃበሻው ምድር በየዘመናቱ የሚዘንበው የመከራ ዶፍ ቋሚን አደንዝዞ የሞተውን አስረስቶ እኔ እሻላለሁ በሚል የዘር ፓለቲካ ምድሪቱን ሲኦል እንዳረጋት ዓይን ያለው ያያል።

    1. Tesfa

      It appears to me, you are as confused as the preachers that are shouting and yelling to multitudes of people with out any merit or result around the globe. The claim of the Bible must be tested. And it’s being tested by the old and the new generations. I strongly believe 90% of what we hear is rubbish. How do I know this? I suggest to you, to check their words against their actions. It is totally different. It is like a Physician telling a patient not to smoke and drink while he is indulging in it.
      Karl Marx once said “Religion is the opium of the people”. I do agree with him. People are duped. However, I will like to make a great distinction between Faith and Religion. The two are entirely different. Prosperity teaching is a systematic way of gleaning/fleecing resources from the most vulnerable people. And that is what we are witnessing on the pulpit as well in our daily walks. That’s what I call “stunning idiotic” to be taken advantage by the very person who is teaching you heaven to be your home.

  3. Netsanet Miftah

    Thank you Dr. Dereje Kebede for your deep concern and briefings on new coming spritual practices at Churches.

Leave a Reply