
ብልጽግና የኢህአዴግ ብስባሽ በመሆኑ ብልጽግና ፓርቲ ሀገሪቱን እስከመራ ድረስ የአማራ ሞት ሊቆም አይችልም ሲሉ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ገለጹ ከአሻራ ሚዲያ ጋር በወቅታዊ የሀገሪቱ ችግር ጋር በተያያዘ ሚዲያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ታዋቂው ፖለቲከኛ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አሁን ላይ በየአቅጣጫው የአማራው ማህበረሰብ ሞትና ሰቆቃ የበዛው ህገ መንግስቱን የማስፈጸም ዋነኛው ማሳያ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ህገ መንግስቱ ለአማራ ህዝብ ውክልና የማይሰጥ በመሆኑ እና በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ አማራዎች መገደላቸውና መፈናቀላቸውየኦሮሚያ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ህገ መንግስቱን የማስፈጸም ብቃት ማረጋገጫቸው ነው፡፡ በመሆኑም ብልጽግና ፓርቲ እና አሁን ላይ ስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት እስካሉ ድረስ በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የዘር ማጥፋት፤የሀብት ንበረት ዘረፋ፤ማቃጠልና ማፈናቀል እየጨመሩ ይሄዳሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የተከበራችሁ የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮቻችን ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ከታች የምትመለከቱትን ሊንክ በመጫን እንድትከታተሉት እንጋብዛለን https://youtu.be/3xJG0npUtTU
Source: Link to the Post