ብልጽግና የኢትዮጵያ የነገ ተስፋ የሆኑ ልጆቿን የሚከፋፍል አጀንዳ በአዲስ አበባ እያራመደ ነው።አስገራሚው ነገር የፓርቲው የሌሎች ክልል አባላት ይህንን ሃገር በታኝ አጀንዳውን ለማስቆም ምንም ጥረት ሲያደርጉ አለመታየታቸው ነው።

ድርጊቱ ምንም ዓይነት የጎሳ ፖለቲካ ቅብ ለመቀባት ቢሞከር የድርጊቱ ዋና ግብ የኢትዮጵያን መጪ ትውልድ መከፋፈል እና ኢትዮጵያን ማዳከምን መድረሻው ያደረገ የመርዝ ብልቃጥ ነው። በምድር ላይ ያለ ማንም መንግስት የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማውን የሚገዳደር  የአንድ ክልል ሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር ተማሪዎቹ እየዘመሩ እርስበርሳቸው እንዲከፋፈሉ ሲያደርግ ተሰምቶ አያውቅም።=========ጉዳያችን ምጥን=========አንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ብልጽግን በጎሳ ፖለቲካ የማያምን እንደሆነ ሲናገሩ ” እኛን ብልጽግናዎችን አትከፋፍሉን።እኛ ብልጽግናዎች ከዘር የተከፋፈለ አስተሳሰብ የጸዳን ነን። እኛ የምንሰራው ለአንዲት ኢትዮጵያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply