ብልፅግና ፓርቲ ለምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች ትብብር እንዲያደርግ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ፡፡ምርጫ ቦርድ ዛሬ መስከረም 02/2015 በሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤው፣ የብልጽግና ፓ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/RNxeU86GSZwYM8IweLR5B3k2fpztBV4TTUgygwvShmKVUCEznGlgQUlU6cHlbOWe8lyvw6l-9TrwvO7JWskXSoQfL8xyqP5pnaEnq3eo4oJ4-Padi1oEf9ZOzER4FYCW2DIkeNWuU-dJksVXRudGZEKmBf4EV_mJBWetsbxWRlqHp7GE9gUrfdHteQqw9qUKzTh2IHkp3cGxEbRmyUEPk5f5nDg-IJxe-6Ep-Gkvi8kek2AbyLYgrNWF85gvpkthXm2WVjEOs_Pe4JeAo3SInakNG_s2kco8rLyR0lmFhBmGlhkHZuRrm1KeM3LTIYlpvlK5tbGspoChGyoJeNvGuA.jpg

ብልፅግና ፓርቲ ለምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች ትብብር እንዲያደርግ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ፡፡

ምርጫ ቦርድ ዛሬ መስከረም 02/2015 በሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤው፣ የብልጽግና ፓርቲ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ. ም ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ በጥልቀት መርምሮ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡

በደብዳቤው የመረጃ ልውውጦች እንደነበሩ ያስታወሰው ቦርዱ ጉባኤውን በተመለከተ ከህግ እና ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ከቦርዱ ታዛቢዎች ከቀረቡ ሪፖርቶች አንጻር መክሮ ውሣኔ አሳልፏል፡፡

በሶስት ነጥቦች ስር የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈው ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤው ካካሄዳቸው ምርጫዎች ጋር በተያያዘ የተስተዋሉ ሶስት ክፍተቶችን፡ መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ማስተካከያ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በሚመለከትም ስድስት ነጥቦችን የብልጽግና ፓርቲ እዲያስተካክል ጠይቋል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ቦርዱ የመተባበር ግዴታን በተመለከተ ሲል ህግ አጣቅሶ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣጥ እንዲረዳው ብልጽግናን ጨምሮ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ (Duty to Cooperate)እንዳለበት አስታውሷል፡፡

በመሆኑም ፓርቲዎች በሚያካሂዷቸው ጉባዔዎች ላይ የህግ እና የደንቦቻቸው ተፈጻሚነትን ለማረጋገጥ ይረዳው ዘንድ፣ የቦርዱ ባለሙያዎች የተንቀሳቃሽ ምስል/ቪዲዮ እንዲቀረፅ የአሰራር መመሪያ ሰጥቶ እየሰራ ቢገኝም፣ ከዚህ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ከመጋቢት 2 እስከ 4/2014 ዓም በቦርዱ የተመደቡ ባለሙያዎች ሂደቱን ለመቅረጽ ተከልክለዋል ብሏል ቦርዱ፡፡

በመሆኑም ብልጽግና ከቦርዱ በተፃፈለት ደብዳቤ ይህ ተቀባይነት የሌለውን ተግባር እንዳይደግ ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ቦርዱ ወስኗል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

መስከረም 02 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply