“ብልፅግና ፓርቲ አማራን ከዘር ጭፍጨፋ ለመታደግ አቅም ሳይሆን ፍላጎት ጭምር የለውም” ሲሉ አቶ ማሙሸት አማረ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም…

“ብልፅግና ፓርቲ አማራን ከዘር ጭፍጨፋ ለመታደግ አቅም ሳይሆን ፍላጎት ጭምር የለውም” ሲሉ አቶ ማሙሸት አማረ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም…

“ብልፅግና ፓርቲ አማራን ከዘር ጭፍጨፋ ለመታደግ አቅም ሳይሆን ፍላጎት ጭምር የለውም” ሲሉ አቶ ማሙሸት አማረ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፈለገ ግዮን በገጹ እንዳሰፈረው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ማሙሸት አማረ “ብልፅግና ፓርቲ አማራን ከዘር ጭፍጨፋ ለመታደግ አቅም ሳይሆን ፍላጎት ጭምር የለውም” ሲሉ ገልፀዋል። በተጨማሪም “የአማራ ህዝብ ራሱን መጠበቅ ብቻ ነው ያለበት። አፈ ቀላጤዎች የሚያወሩትን መስማት የለበትም። ጉራ ፈርዳ ላይ አማራን በደብዳቤ ያስጨፈጨፈው ሽፈራው ሽጉጤ ነው።” በማለት አውስተዋል። “ዛሬ ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነው። በዚህ ጨካኝ ስር የነበሩ አመራሮች ሞዴላቸው እሱ ነው።” ያሉት አቶ ማሙሸት በኢህአዴግ ቁጥር አንድም ሆነ ቁጥር ሁለት አማራን ከገደልክ፣ ካፈናቀልክ፣ ካዋከብክ ስልጣን ታገኛለህ ሲሉም አክለዋል። ይሄ የኢህአዴግ ስርዓት ህጋዊ ስሪት ስለመሆኑ የጠቆሙት አቶ ማሙሸት ብልፅግና የሚባለው ቁጥር ሁለት ኢህአዴግም አማራን ከዘር ጭፍጨፋ ለመታደግ አቅም ሳይሆን ፍላጎት ጭምር የለውም ሲሉ ገልፀዋል። የመረጃ ምንጭ ፈለገ ግዮን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply