ብልፅግና ፓርቲ አምስት ዓመት እንዲገዛን ድምፃችንን አንሠጥም! የኮንትራት ውል አንፈርምም! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

‹‹አሣ ጎርጎሪ ዘንዶ አወጣ፣ የሰው ፈላጊ የራሱን አጣ!!!››

ኦዴፓ ብልፅግና ቀን በምርጫ ብቻ! ማታ በሜንጫ ብቻ! በጎችን ከተኩላና ከአንበሳ ምረጡ አሏቸው!

 

የተመረጠና ያልተመረጠ የብልጽግና መንግሥት…. የተቀሸረና ያልተቀሸረ  ብልፅግና

2013/ ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት 476 (አራት መቶ ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ብር ውስጥ 176 (መቶ ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ብር (37 በመቶ) ለክልሎች ድጎማ፣ 160 (መቶ ስልሳ) ቢሊዮን ብር (34 በመቶ) ለካፒታል በጀት፣ 133 (መቶ ሠላሣ ሦስት) ቢሊዮን ብር (28 በመቶ) መደበኛ በጀት እና 6 (ስድስት) ቢሊዮን ብር ለዘላቂ ልማት የተደለደለ ነው፡፡ በመደበኛው በጀት ውስጥ የሚካተተው የፌዴራልና የክልሎች የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ደሞዝ፣ ወዘተ ያጠቃልላል፡፡  ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት በዋናነት የሚገኘው ከህዝብ ከሚሰበሰብ ግብርና ታክስ ከፋዬች ኢትዮጵያዊያን ነው፡፡ ግብር ከፋዬች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህይወት የመኖር መብቶቹ፣ ኃብትና ንብረት የማፍራት መብቱ፣ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራት ነጻነቱ፣ ወዘተ የሚጠበቅለት  በኢፊድሪ መከላከያ ሠራዊት (ኮማንድ ፖስት) በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደሞዝና አበል ሲሆን ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቦታው በዘር ፍጅት በየቦታው ይታረዳል፣ ይቆስላል፣ ይዘረፋል፣ ይሰደዳል፡፡ እንደ ዘመነ ዬዲት ጉዲት፣ ዘመነ ዐብይ ጉዱ ተሸጋግረናል፡፡በመሆኑም ገዳዬቻችንን አሠልጥኖና አስታጥቆ ለሚልክብን የአብይ አህመድ አገዛዝ ግብር መክፈልን በእንቢተኝነት ማሳየት ይኖርብናል፡፡ ከአራጆቻችን እራስን የመከላከል ተፈጥሮዊ መብታችንን በመጠቀም ማንኛውም ዓይነት ጥቃትንና የዘር ፍጅትን ለመከላከል በጎበዝ አለቃ  መደራጀት የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡   

 

በደም የታጠበና ያልታጠበ መንግሥት …‹‹በምርጫ ብቻ!!!›› ‹‹በሜንጫ ብቻ!!!››

የኦዴፓ ብልፅግና መንግሥት በህዝብ ሳይመረጥ በደም የታጠበ ፋሽስታዊ ሥርዓት በትግራይ ክልላዊ መንግስት 52000 ሰዎች ተገድለዋል፣ ሦስት ሽህ ሃያ አራት ህፃናት ወላጆቻቸው እንደጠፉባቸው እንዲሁም ስምንት መቶ ሴቶች ተደፍረዋል፣ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ በትግራየይ የገጠር ከተማዎች ነዋሪዎች መሠረታዊ አቅርቦቶች እንደማይደርሳቸው ዩኒሲኤፍ ሪፖርት አረጋግጦል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹በምርጫ ብቻ!!!›› በሚል ፋሽን ምርጫ አካሂዶ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዘረጋሁ ብሎ ለዓለም መንግሥታትና ህብረተሰብ ለማሳወቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጎምጅቶል፡፡  ሆኖም የኢትዮጵያን ህዝብ መናቅ ካልሆነ ቃሉን ለበላ አብይ አህመድ እንኳን የምርጫ ካርዱን  ኦርጅናሉን ቀርቶ ፎቶኮፒውን አይሠጠውም፡፡

 

‹‹የኢዜማ ሚስጥራዊ ሰነድ›› ሆን ተብሎ የተለቀቀ ሰነድ፣ የኢሳያስ መፈንቅለ አገዛዝ በኢትዮጵያ

‹‹የኢዜማ ሚስጥራዊ ሰነድ›› የሻቢያ የኢሳያስ መፈንቅለ የልጅ መንግስት በኢትዮጵያ በምርጫ ተአቅቦ ማግስት የኦሮሙማ መጭው የብልፅግና የብርሃን ዘመን ወደ ጨለማ ዘመን መሸጋገሪያ ሰነድ መሆኑን ብርሃኑ አንዳርጋቸው በጨለማው አንድርጋቸው አብይን የታደጉበት የኦሮሙማ ሥርዓት እንዲያቆጠቁጥ ተመኙ ሆኖም አንድም በምርጫ ድምፀ ተአቅቦ የአብይ መንግሥት ተፈረካከሰ ሁለትም በትግራይ ጦርነት በዓለም መንግሥታት ተጋለጠ፡፡ ሦስትም የኦሮሙማ ሽፍታ ዝናር በቅፊ ሠራዊት እያደረገ ላለው የዘር ፍጅት በሻብያ ሠራዊት ሊቀለበስ እንደሚችል ስጋት ሆኖባቸዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በሻብያ ፊት አውራሪነት ተልዕኮ ተሠጥቷት ሃገር የገባ ጦር መሆኑን የለማና አብይ ዞንቢ  ጭንቅላት በሴራ መጠለፋቸው ግን አላወቁትም ነበር፡፡  ኢሳያስ የኦሮሙማን ዘረኛና ተረኛ የአብይ አህመድ አራጂ መንግሥትን ቢያስቆም የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፉን ለኢሳያስ በመስጠት አብይን አሮጌ ቁና አያረገውም አይባልም፡፡

አብይ አህመድ ‹‹አሣ ጎርጎሪ ዘንዶ አወጣ፣ የሰው ፈላጊ የራሱን አጣ!!!›› እንደሚባለው ተረት የሥልጣን መንበሩን ተነጥቌል፣ከመዝናኛ ፓርኮቹ በስተቀር ሌላ የተሠፈረለት ስራ የለም፡፡ ሠራዊቱም፣ ደህንነቱም፣ ኦሮሙማም ኦሮማይ! ኦሮማይ!  ሆኖል፡፡ አብይ ወያኔን በሻብያ አስመታሁ ብሎ ያምናል፡፡አብይ ሻብያ ግባ ሲባል የሚገባ ውጣ ሲባል የሚወጣ የገንዘብ ቅጥረኛ (Mercenary) መስሎት ነበር፡፡ ሻብያ ጥንትም ዛሬም የሚጫወተው የፖለቲካ ሴራ ተገምዶ በጦርነት ሲሸነፍ፣ እንደ ዘንዶ ሃዘኑን ውጦ ከተኛ ሃያ አመታት ታግሶ አፈር ልሶና አመድ ቀምሶ ወያኔን ደቁሶ፣ ኦሮሙማውን ቆንጆውን ዐብይ ማድያት ሳያለብሰው አይለቀውም፡፡ ኢሳያስ ‹‹የዘር ፖለቲካ ተው ብዬ መክሬቸው ነበር›› ይላል አልሰማ አሉ፣ በየቦታው የዘር ፍጅት ቀጥሎል፡፡  ዛሬ አብይ በአንዳርጋቸውና ብርሃኑ የሚዘወር ፖለቲካ በሚሠፈርለት የሰነድ ቀለብ፣ አቤት ሲሉት ወዴት ማለት ጀምሮል፡፡ እንግሊዙ አንዳርጋቸውና አሜሪካው ብርሃኑ ሚስትና ልጆቻቸውን ጥለው፣ በኢትጵያ ህዝብ ፍቅር ነደው፣ የሃገር ፍቅር አቃጥሎቸው  በምድረ ኢትዮጵያ ቄጤማ ጉዝጎዝ ጎዝጉዘው፣ ዱአ እያደረጉ ሰነድ በማዘገጋጀት ድሮ ማርክሲዝምን ሌኒኒዝም እየጠቀሱ ዛሬ ‹‹እርካብና መንበር›› እያጣቀሱ ለህዝብ ፖለቲካ እየካደሙ ‹‹በንጉስ አጫዋችነት›› እንደ ጨዋ ሰዉ ካባ እየለበሱ፣  ጨዋታ እያሳመሩ፣ ፍልስፍና በአረቄ እያስጎነጩ፣ የፖለቲካ ካድሬ እንደ በግ እየመለመሉ ቀሪ ህይወታቸውን ለመኖር የነፍስ ኮንትራት ከኢሳያስ ጋር ፈርመዋል፡፡ ሥጋቸው ቢያረጅበት፣ ነፍሳቸውን ገዛቸው እነሱም ሸጠዋል!!! ሁለቱም ጥላ የላቸውም ለምን ነፍሳችሁን ሸጣችሁለት ብሎ የጠየቃቸው ጋዜጠኛ ባያገኙ እንደእናትና አባት ሆኖ በዛ ክፉ ቀን ቀለብ ይሠፍርላቸው የነበረው የኢሳያስ አፈወርቂ ነበር፡፡  ኢሳያስ በሪሞት ኮንትሮል ከአስመራና ምፅዋ ጉርጉሱም እየተዝናና ሁሉን አዳሜን ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ እንበል አስራሁለት!!! እግዚኦ ማህርነ ክርስቶስ የፖለቲካው ሴራ እንዲገለፅልህ የአባቶች ጸሎትና ሁለት ባለ አሥራምስት የአቦ ፀበል  ያስፈልጋል፡፡

 

‹‹የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ከማሺ ዞን የሚገኘውና ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙበት የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ፣ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን የደረሱት መረጃዎች ያመላክታሉ። በርካታ ነዋሪዎች፣ የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች መሸሻቸውን ኮሚሽኑ ተረድቷል። ታጣቂ ቡድኑ የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችን ማቃጠሉን፤ ነዋሪችን፣ የወረዳውን እና የዞን አመራሮችን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችን መግደሉን እና ማገቱም ተገልጿል። ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በአቅራቢያው ያለው የፀጥታ ኃይል ከአቅሙ በላይ እንደሆነና ተጨማሪየተላከው ኃይልም ወደ አካባቢው እንዳልደረሰ ይገልጻሉ።ይህ ክስተት በክልሉ የቆየው የጸጥታ ችግር እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት የሚያሳድር ነው።ኢሰመኮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ነው። ኮሚሽኑ መንግስት በአፋጣኝ የአካባቢው እና የክልሉን የፀጥታ ኃይል እንዲያጠናክርና እና ተጨማሪ የሰዎች ሞት እና የከፋ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰት እንዲከላከል ጥሪውን ያቀርባል::››……….(1)

ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን በወለጋ፣ በጅማ፣ ጭፍጨፋ  ለማስቆም እንዲሁም የሻሸመኔ፣ አጣዬ፣ ካራቆሬ፣ ማጀቴ ከተሞች ቃጠሎን ያደረጉ አራጂ ወንጀለኞችን ለፍርድ አቅርቦ ይህን ዘረኛና ተረኛ ሥርዓት በሥርዓት ለውጥ መቀየር ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡  ወንጀለኞቹን ለዓለማቀፍ ፍርድ ቤት ለፍርድ ለማቅረብ ጅምላ ፍጅትንና ዘር ማጽዳትን ወንጀለኞችን መረጃ በማሰባሰብ ከኢትዮጵያ ፈጽሞ ኣስኪጠፋ ድረስ ካገር ውጪ የተቋቋመውን ስብስብ በገንዘብ፣ በዕውቀትና ተግባራዊ ድጋፍ በማድረግ ወንጀለኞቹ ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እስኪቀርቡ ድረስ መታገል ይጠይቃል፡፡ በአገር ውስጥም በጎበዝ አለቃ እየተደራጁ እራስን መከላከል የተፈጥሮ ግዴታ ሆኖል፡፡

ራዕይ ለኢትዮጵያ በመጪውን ምርጫ ኦዴፓ ብልፅግናን ፓርቲን ባለመምረጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ከምርጫ ራሱን እንዲያገል አሳስቦል፡፡ ራዕይ ለኢትዮጵያ መግለጫ መሠረት፡-

1-ኢትዮጵያን እያመሠ ያለው የኦሮሙማ እኩይ ተግባር አጋዥ መሆኑን በማመን የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን ዘር ተኮር ድርጊቶች አጥብቀን እናወግዛለን፡፡

2-መጪው ምርጫ ፋይዳ-ቢስ መሆኑን በመገንዘብ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጪውን ምርጫ እንዳይቀበልና እውነተኛ ዴሞክራሲና የተጠናከረች ኢትዮጵያን ለመመሥረት እውን የሚያደርግ የሽግግር መንግሥት በአስቸኳይ እንዲቌቌም እንዲታገል ጥሪ እናደርጋለን፡፡

3- የዘር-ጥፋት ሰለባ ለሆኑት ወገኖቻችን ያለንን ጽኑ ሃዘን እየገለጽን፣የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከልና ለማጋለጥ እየሠሩ ላሉት ቡድኖች አጋርነታቸንን እናረጋግጣለን፡፡ በተለይም እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ለማጋለጥ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱትን እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንየዘር ጥፋት መከላከያ ድርጅት (ኢተክዘድ፣OTAGE) በመሳሠሉ ድርጅቶች የኦሮሙማ አሸባሪ ቡድን አባላትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት እናወድሳለን፡፡

4- ኦነግን ሕወሓትንና ሌሎችንም በኢትዮጵያ ያሉትን የሽብር ቡድኖች እያወገዝን እነኝህን ጽንፈኞች በጋራ ለመዋጋት ለመላው አገር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በተለይ የትግራይና የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉን በእኩልነት በመሠለፍ ለአንድነት ለነፃነትና ለዴሞክራሲ በሚደረገው ትግል የራሳቸውን ሚና እንደሚጫወቱ እናሳስባለን፡፡

5- እንደ ሕወሓት ኦነግን እና ሌሎች የኦሮሙማ አክራሪ ጽንፈኛ ቡድኖች በሚቀሰቅሱት አመጽና ሽብር በአፍሪካ ቀንድ ሊፈጠር የሚችለውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥፋትና ቀውስ እንዳይከሰት ለመከላለክና ይኽንንም ጥፋት ለመታደግ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን በማገዝ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ለዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ጥሪ እናደርጋለን በማለት ውሳኔዎች አስተላልፎል::……… (2)

በተመሳሳይ በሞረሽ ወገኔ መግለጫ መሠረት ‹‹ዐማራው በፋሽሽታዊ አገዛዙ አውራ ጠላት ተደርጎ ለዘር ማጥፋትና ለዘር ማጽዳት ወንጀሎች በሰፊው የተጋለጠው ኢትዮያዊነትን መለያው በማድረጉ ነው። የጣልያንና የሌሎች የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችን ፍኖተ ካርታን የፖለትካ ፕሮግራማቸው ያደረጉት የትግሬ/ወያኔና ኦነግ በሀገር ላይ የጫኑት አራዊተ ሕገ መንግስት ዐማራን ለማጥፋት የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑ በገሃድ ሲታይ ሶስት አስርተ ዓመታት ሊሆነው ነው። ይህ የአፓርታይድ ስርአት የተቀየሰበት ኢትዮጵያን የማድከምና የማፈራርስ ጉዞ በአብይ አህመድ አሊ የሦስት አመት አጭር የነውጥ ጊዜ እየተፋጠነ ነው። በውጭም ሆነ በውስጥ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ህልውና ፈተና ላይ ወድቋል። ስለሆነም ይህን ህገ አራዊት መቀየር አለበት፣ የሚሉ የዐማራና ህብረ ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ከአገዛዙ የምርጫ ትያትር እራሳቸውን አግልለው፣ የአብይ አህመድ የኦሮሚማ ካምፓኒ ከስልጣን ወርዶ ሁሉን አሳታፊ የሽግግር መንግስት ይመሰረት ዘንድ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርብላቸዋለን።….ብአዴን / አዴፓ የወያኔ አሽከር ሆኖ አብዮታዊ ዲሞክራሲን እያቀነቀነ 27 ዓመት እያስገደለ የኖረ፤ የዐማራን ሕዝብ ስነልቦና ያልተላበሰ፤ ስለሰብዓዊ መብት ግንዛቤ የሌለው፤ ሎሌ እንደሆነ ይታወቃል። አዴፓ ዛሬም ጌታ ቀይሮ የአብይ አህመድን የመደመር (ገዳ፣ሞጋሳ) የወረራ ሥርዓት ተሸካሚ ሆኖ የጨፍጫፊው የኦዴፓ/ ኦሮሞ ብልፅግና ጉዳይ አስፈፃሚ በመሆን ስለሚሰራ፤ ከሽመልስ አብዲሳ የወረራ አካል ጋር ስምምነት ላይ ደረስን እያለ ከማዘናጋት ውጪ እንደ ዐማራ ክልል መንግስት ሕዝቡን እንደማይታደግ በተደጋጋሚ አስመስክሯል። ›› ……..  (3)

 

የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት መሪ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት ጠርንፎ በመያዝ ህዝቡን በመግደል፣ በማሰር፣ ንብረትና ኃብቱን በመዝረፍ ላይ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያ ከአስር ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ፈት በመሆናቸው በኦነግ ፖለቲከኞች የተፈጠረላቸው የዘረፋ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሃያ ሦስት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮችን በመዝረፍ የኦሮሙማ ማድረግ፣ መንግሥታዊ ድርጅቶችን ንብረትና ኃብት፣ መኪኖች ወዘተ መዝረፍ፣ በኦሮሚያ የሚገኙ ኢንቨስተሮችን መዝረፍ ቀሪውን ድርጅቶች እንደ ሻሸመኔና አጣዬ ከተማዎች ማቃጠል፣   ወዘተ  የጥገኛ ተዋሲያን የወሮበላ፣ የጠርጎ በላ የሽፍታዎች ህጋዊና ህገወጥ መንግሥት ያለሥራ በዘረፋ ፀጉራቸውን እየጎነጎኑ፣ ጥርሳቸውን እየፋቁ በእጅ ስልክ በሞባይል ስልፊ እየተነሱ  በመላክ ዘመናዊ ሰው አራጆቹ ህጋዊ የሆኑ መስሎቸዋል፡፡

 

ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ የምንመርጠው ባለፈው ሦስት አመታት ምን ስለሠራ ነው?

ከመጋቢት ሃያ አራት 2010 እስከ 2013ዓ/ም  ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ መሪ የዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን የኦሮሚያ ምድር በደም ታጠበች፣ በህይወት የመኖር መብት ጠፋ ጣረ-ሞት በኢትዮጵያ እንዳንጃበበ ይገኛል፡፡

  • ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ካማሽ፣ መተከልና አሶሳ ዞኖች ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም ውስጥ 750 ሰዎች ስጋቸው ተበልቶል ደማቸው ተጠጥቶል፣ 265405 የአማራ ህዝብ ብዛት የነበረ ሲሆን በሦስት አመታት ውስጥ 221347  አማራዎች ተፈናቅለዋል፣ 2581 ተገድለዋል፣ 905 የቆሰሉ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 40572 አማራዎች በክልሉ ውስጥ ይኖራሉ፡፡
  • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወለጋ፣ አርሲ ዞን፣ባሌ፣ ኢሉባቡር፣ ጅማ፣ ዝዋይ ኢተያ ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም 2465 ሰዎች ተገድለዋል፣ 1905 ሰዎች ቆስለዋል፣ 839645 ሰዎች ተፈናቅለዋል
  • በደቡብ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም 641 ሰዎች ተገድለዋል፣ 209 ሰዎች ቆስለዋል፣ 105000ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡…………(4)

በህገመንግሥቱ መሠረት ባለፈው ሠላሳ አመታት በወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት ህወሓት ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴን አመራሮች እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ ኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ)፣ የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ(አዴፓ)፣ ፣ የደቡብ ብልፅግና፣ ትግራይ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ቢኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሲዳማ፣ ሃረሪ፣ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰ የስብዓዊ የሰው ልጆች ላይ የተፈፀሙ  ወንጀሎች የዘር ፍጅት፣ ኢስብአዊ ድርጊት የፈፀሙ ወንጀለኞች  በህግ ፊት መቼም ቢሆን መቅረባቸው በህገ-መንግሥቱ የተረጋገጠ ይርጋ የሌለው በመሆኑ  አንድ ቀን ከመጠየቅ እንደ ቀይ ሽብር ወንጀለኞች አይቀሩም እንላለን፡፡

 

ዴሞክራሲ እንዲለመልም እችኑ ማህበራዊ ሚዲያችንን አትዝጉብን!!!  አራጆቹን ከማስተማር ሌላ ምን አለንና!!!

 

ምንጭ

Leave a Reply