ብልፅግና ፓርቲ  ከሀገሪቱ ቁጥር አንድ መሰረዝ  የነበረበት   ፓርቲ ነው – አቶ ልደቱ አያሌው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም) ብልፅግና ፓርቲ  በውህደት ከተመሰረተ ወዲህ ጠቅላላ ጉ…

ብልፅግና ፓርቲ ከሀገሪቱ ቁጥር አንድ መሰረዝ የነበረበት ፓርቲ ነው – አቶ ልደቱ አያሌው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም) ብልፅግና ፓርቲ በውህደት ከተመሰረተ ወዲህ ጠቅላላ ጉ…

ብልፅግና ፓርቲ ከሀገሪቱ ቁጥር አንድ መሰረዝ የነበረበት ፓርቲ ነው – አቶ ልደቱ አያሌው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም) ብልፅግና ፓርቲ በውህደት ከተመሰረተ ወዲህ ጠቅላላ ጉባዔ፣ ማዕከላዊ እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴም በጉባኤ አላስመረጠም፡፡… የፓርቲውን ፕሮግራም እና ደንብ በጉባዔ አልፀደቀም፡፡ የምርጫ ቦርድ ታዛቢነትም የለበትም ያሉት አቶ ልደቱ እኛ ለ21 ዓመታት በትግል ያቆየነውን ፓርቲ መሰረዝ ሚዛናዊ አይደለም ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ ህግ ካለ በቁጥር አንድ መሰረዝ ያለበት ብልፅግና ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡ ነገር ግን ህግ ስሌለ ከሚጠበቅብን 10ሺ የመስራች አባላት ፊርማ 17ሺ ይዘን መሰረዛችን ፍፁም ከሞራል ከህግም ጋር የሚጋጭ ነው ብለዋል፡፡ ኢዴፓ ከ1992 ዓም ጀምሮ በምክንታዊነት እና ሶስተኛ መንገድ የሚል አማራጭ በመከተል ይታወቃል፡፡ ኢዴፓ በምርጫ 97 በኢትዮጵያ ማዕበል የፈጠረ እና መሪው አቶ ልደቱም ማንዴላ እስከ መባል ደርሰው ነበር፡፡ የቅንጅት መከፋፈል እና የተዛባው ፕሮፖጋንዳ ማን ትክክል ማን ስህተት መሆኑ በግላጭ ሳይለይ አቶ ልደቱ ሲወቀሱ ከርመዋል፡፡ አቶ ልደቱ የለውጡ መሪዎች ለመተቸት የማይበቁ ልፍስፍሶች ናቸው ብለው ነበር፡፡ ሀገሪቱ በዚህ መንገድ ፈፅሞ መጓዝ የለባትም በማለታቸውም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply