ብሔራዊ ባንክ የብር ቅያሬውን በተመለከተ ማሳሰቢያ ሰጠ !! ================================== አሻራ ሚዲያ መስከረም 25/2013 ዓ.ም ባህርዳር ከ100 ሺህ እስከ 1 ነ…

ብሔራዊ ባንክ የብር ቅያሬውን በተመለከተ ማሳሰቢያ ሰጠ !! ================================== አሻራ ሚዲያ መስከረም 25/2013 ዓ.ም ባህርዳር ከ100 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር አሮጌውን የብር ኖት በእጃቸው የያዙ አካላት እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲሱ የብር ኖት እንዲቀይሩ ብሄራዊ ባንክ አሳሰበ። አሮጌውን የብር ኖት በአዲሱ የብር ኖት ለመቀየር መንግስት የ90 ቀናት የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ የሚታወስ ሲሆን ከ100 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር አሮጌ የብር ኖት ለመቀየር የተቀመጠው የጊዜ ገደብ 30 ቀናት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ አሮጌውን በአዲሱ የብር ኖት የመቀየር ስራው መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ከ100 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር አሮጌውን የብር ኖት የመቀሪያ ጊዜም ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ተብሏል። በመሆኑም ህብረተሰቡ በመንግስትም ሆነ በግል ባንኮች በእጃቸው የሚገኘውን አሮጌውን የብር ኖት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲቀይሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply