ብሩንዲ እስር ቤት ውስጥ በተነሳ ቃጠሎ 38 እስረኞች ሞቱ

https://gdb.voanews.com/18EC46D2-7C5B-404C-BF83-750616739543_w800_h450.jpg

ብሩንዲ ዋና ከተማ ቡጅምቡራ ውስጥ በሚገኝ ዋነኛው እስር ቤት ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ 38 እስረኞች መሞታቸውን የቡሩንዲ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ፡፡ በቀጥታ አስተያየት መስጠት ያልፈለጉ አንድ ባለሥልጣን ለቪኦኤ በቴክስት መልዕክት እንዳስታወቁት ኃላፊዎቹ በወሰዱት አስቸኳይ እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ማትረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡ 

የብሩንዲ የቤቶች ጉዳይና የማህበረሰብ ደህንነትና ልማት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እሳቱ የተነሳው እስረኞቹ በእስር ቤቱ ውስጥ ካለው ኤሌክትሪክ ለክፍላቸው የሚሆን መብራት ለመቀጠል ባደረጉት ሙከራ ነው፡፡ 

ይሁን እንጂ የቡሩንዲ ዋነኛው ተቃዋሚ የብሄራዊ ለነጻነት ምክር ፓርቲ መሪ አጋቶን ርዋሳ ለቪኦኤ ዘጋቢ ጀምስ ባቲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠየቅ ለአደጋው አፋጣኝ ምላሽ አለመሰጡትን እንደሚከተለው ይገልጻሉ 

“ይህ እሣት አደጋ ዛሬ ጧት መድረሱ በጣም አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ በጣም የሚያስዛነው እሳት አደጋው የተከሰተው ከሌሊቱ 10 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ የእሳት አደጋ መከላከያዎቹ የደረሱት ግን ዛሬ ጧት ከ12 ሰዓት በኋ ነው፡፡ ያ ማለት ከሁለት ሰዓት በላይ እስረኞቹ ያለምንም እርዳታ ለእሳት አደጋው ተጋልጠው ነበር ማለት ነው፡፡ ”

ሩዋሳ እንደሚሉት ስለ እሳት አደጋው መነሻ መንግሥት የሚለው በገለልተኛ ወገን መጠራት አለበት በማለት እስረኞቹ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመዶቹንና መሳሪያዎቹን ከየትና እንዴት አገኟቸው ብለው ጠይቀዋል፡፡ ከዚህም በላይ በብሩንዲ ያሉት ብዙዎቹ እስር ቤቶቹ ብዛት ባላቸው እስረኞች የተጨናነቁ በመሆናቸውም ይህኛውም እስር ቤት እንዲሁ ከተሰራበት በላይ ከፍተኛ ቁጥር እስረኞችን የያዘ መሆኑን ይገልጻሉ

“ዛሬ ጧት የተቃጠለው እስር ቤት በቅኝ አገዛዙ ዘመን የተገነባ ነው፡፡ እንደሚመስለኝ ይህ ቃጠሎ ሲደርስ የእሳት አደጋ ቢፈጠር መከላከል የሚያስችል ምንም ነገር በቦታው አልነበረም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የጊቴጋ እስር ቤት፣ በብሩንዲ እንዳሉት ሌሎች እስር ቤቶች በጣም ከተጨናነቁት ውስጥ ነው፡፡ እስር ቤቱ ሲገነባ ለ300 ሰዎች አካባቢ እንዲሆን ተብሎ የተሰራ ነው፡፡ የእሳት አደጋው በደረሰ ጊዜ ግን የነበሩት እስረኞች ከአንድ ሺ ሶስት መቶ ሰዎች በላይ ነበሩ፡፡”

Source: Link to the Post

Leave a Reply