ብሪታኒያ አምባሳደሯን ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በጊዜያዊነት አዛወረች

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-2dba-08db474d5763_w800_h450.jpg

ብሪታኒያ፣ ለሁለት ሳምንታት ገደማ የቆየው ውጊያ በሚካሔድባት ሱዳን የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች፤ አምባሳደርዋን ጊልስ ሌቨርንም፣ ለጊዜው ወደ ዐዲስ አበባ ማዛወሯን አስታወቀች፡፡

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኤምባሲውን መዘጋት አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ውጊያ እንዲያከትም፣ ዩናይትድ ኪንግደም የምታደርጋቸውን ጥረቶች፣ አምባሳደሩ፣ “ዐዲስ አበባ ኾነው ይመራሉ፤” ሲል አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply