“ብራና” የተሰኘ  ገሚስ የሙዚቃ አልበም ለምርቃት በቅቷል።በወጣቱ የዘፈን እና የግጥም ፀሃፊ በሆነው እብነ ሀኪም(ሚኪያስ) የተሰራው  ይህ አልበም  ግጥምና ዜማው ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀው በራሱ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/fQcrgouNUadyiLjqSMRlPnxaLMWfK2132sGV226nHM39ZjaaCKUVhTWDaIVi4IYbmOXYF7BTvbuq92pBnPJrKgmF9TTi604cwJmvHslV16FFmUezDyT50wO0jYUagAGBAkqcEUG3yn66P2ioJhxMR5W5thWPAGG_Ab3zWAs1LAzQu-SgaHfx5G9PqeVJgv2hymX8Y3GEx80m7tQT6MGZUDEXphn4BoKa8_eaaAUme3YQDbGT1VZCyhDmwCJNifyfL_CwRiTlyVlDq_bZY0LQVt8hnR9kt6-6Ly-llj_ZIV3VzVRhBrOdVPv5SSlJWp9aytsWHZuGwsbE9xDrWZtSqQ.jpg

“ብራና” የተሰኘ  ገሚስ የሙዚቃ አልበም ለምርቃት በቅቷል።

በወጣቱ የዘፈን እና የግጥም ፀሃፊ በሆነው እብነ ሀኪም(ሚኪያስ) የተሰራው  ይህ አልበም  ግጥምና ዜማው ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀው በራሱ በአርቲስቱ እንደሆነም ተገልጿል።

መሉ ስራው በባና ሪከርድስ እንደተሰራ ተገልፆ  አልበሙ ስድስት ትራኮችን የያዘ ሲሆን   ስድስቱም ክሊፕ እንደተሰራለት ገልፀዋል።

ለዚህ አልበም መብቃትም  ባና የተሰኘ የሙዚቃ አቀናባሪ ተቋም  ጉልሁን ድርሻ እንደተወጣ ተገልፆ ከአለም አቀፉ ሶኒ አፍሪካ  የሙዚቃ ድርጅት ጋርም በጋራ እንደተሰራ ተነስቷል።

“ብራና” ሀገር በቀል ቃል ሲሆን ሁሉም ሰው አይምእሮው ያመላለሰውን ልቡ የወለደውን ሃሳብ እንዲያሰፍርበት ለሁሉም የተሰጠ  መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል ።

ሙዚቃውን ለአድማጭ ለማብቃት  አራት አመታትን እንደወሰደም  ተገልጿል።

ይህ የሙዚቃ ስብስብ በአንድ የቆሎ ተማሪ ህይወት ላይ በሚያጠነጥን መልኩ የተሰራ ሲሆን፤ 

በውስጡም ብራና፣ዬኔታ፣ቃል ብቻ፣ገላ፣ይሁና እና ጉድ ነው የሚሉ  ትራኮች እንደሚገኙበትም ሰምተናል።

በለአለም አሰፋ

ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply