ብራዚል ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ከዛሬ ጀምሮ ወደ በረራ ልትመልስ ነው

ብራዚል ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ከዛሬ ጀምሮ ወደ በረራ ልትመልስ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብራዚል ከዛሬ ጀምሮ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አገልግሎት መስጠት ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች፡፡

ይህንን ያለው የሀገሪቱ ጎል የተሰኘው አየር መንገድ ነው ተብሏል፡፡

ጎል የሀገር ውስጥ በረራዎችን በማድረግ በብራዚል ስም ያለው አየር መንገድ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የአየር መንገዱ 140 አብራሪዎች ወደ አሜሪካ አቅንተው ስልጠና መውሰዳቸው ተነግሯል፡፡

በሰባት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ከዛሬ ጀምሮ በ27 መዳረሻዎች ለተጓዦች አገልግሎት እንደሚሰጥ ነው ጎል ያስታወቀው፡፡

ይህንንም ተከትሎ አስተያየታቸውን የሰጡት የአየር መንገዱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሴልሶ ፌሬር ቦይንግ የወሰደውን ማሻሻያ ተከትሎ በማክስ አውፕላኖች እንደሚተማመኑ ነው የተናገሩት፡፡
ከሦስት ሳምንት በፊት ደግሞ ቦይንግ 737 ማክስ በአሜሪካ ዳግም በረራ እንዲጀምር እንደተፈቀደለት ተሰምቷል፡፡

ቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላኖቹ በአምስት ወራት ልዩነት በኢንዶኔዥያ እና በኢትዮጵያ በተከሰቱ ሁለት አደጋዎች ሳቢያ 346 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ ከመጋቢት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ዓለም በረራ ማቆሙ የሚታወስ ነው፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post ብራዚል ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ከዛሬ ጀምሮ ወደ በረራ ልትመልስ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply