ብራዚል ከዓለም ዋንጫ ተሰናበተች። የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ብራዚል በክሮሺያ በመለያ ምት ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናበተች፡፡በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 1…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/NyJRRI4pPy-govrG0zRCIhEtKj23XTfrer8RAZWAxqA1HihxFgu4_mZ1SYS-SF8LaxemAoJvBN1XoYQ8u4ZFLogwocUG3ud1F0nbdEYsm-eFauVgUSd8dg-KAMCWEjTsAHWUiKoqMhdWDajYD1dvsUTT3UWqWpFewD4ziFGVn0wMiel3QojMqg9Q5WepyBkXpLfOTYfl2x6LxH3rAU1KLAJ3Q91dsAxZr6FbXABEczr0PXnIjtpeKIwaFGwHyBr2z-Jw-FUmv4JWlaZYW8Na_4sBxwU0kCOsm3M41OuKpzbIRfpwAQTPQn3UmRHyYd_R4dt5jr8uHOBrOfL49yihcQ.jpg

ብራዚል ከዓለም ዋንጫ ተሰናበተች።

የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ብራዚል በክሮሺያ በመለያ ምት ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናበተች፡፡

በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ብራዚል እና ክሮሺያ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

በዚህም ክሮሺያ የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗን ብራዚል በመለያ ምት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡

ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን 90 ደቂቃ ያለምንም ግብ ያጠናቀቁ ሲሆን÷በተጨማሪ ደቂቃውም 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም ክሮሺያ 4 ለ 2 በሆነ ውጤት ብራዚልን በማሸነፍ ግማሽ ምጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply