You are currently viewing ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር መሆናቸው ተሰምቷል‼️ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት…

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር መሆናቸው ተሰምቷል‼️ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት…

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር መሆናቸው ተሰምቷል‼️ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ዛሬ ምሽት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤ የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ እንደነገሯቸው ገልፀዋል። ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል። ከአማራ ክልል የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም ፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገ ሙከራ አለመሳካቱን ቢቢሲ አስነብቧል። ©ቢቢሲ

Source: Link to the Post

Leave a Reply