ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከሁለት ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናገሩ።ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ…

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከሁለት ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናገሩ።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ረቡዕ ምሽት ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ ገልጸዋል።

ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል።

ቢቢሲ ይህንኑ በተመለከተ ከአማራ ክልል የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም ፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ሰኞ ዕለት መሰወራቸውን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው ለደኅንነታቸው ሰግተው የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስም ሆነ የፌደራል ፖሊስ ስለጉዳዩ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እንደተነገራቸው ባለቤታቸው ገልጸው ነበር።

ባለፈው የካቲት ወር ላይ ከልዩ ኃይል አዛዥነታቸው ተነስተው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አማካሪነት ሹመት ቢሰጣቸው ሳይቀበሉት መቅረታቸው ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply