You are currently viewing “ብአዴን (የአማራ ብልፅግና) የአማራውን መብትና ህልውና መታደግ የተሳነው ብቻ ሳይሆን ከአማራው ጠላቶች ጋር አብሮ በግልፅ ጠላትነቱን ያረጋገጠ ስለሆነ በክልሉም ሆነ በፌደራል ያለውን የውክል…

“ብአዴን (የአማራ ብልፅግና) የአማራውን መብትና ህልውና መታደግ የተሳነው ብቻ ሳይሆን ከአማራው ጠላቶች ጋር አብሮ በግልፅ ጠላትነቱን ያረጋገጠ ስለሆነ በክልሉም ሆነ በፌደራል ያለውን የውክል…

“ብአዴን (የአማራ ብልፅግና) የአማራውን መብትና ህልውና መታደግ የተሳነው ብቻ ሳይሆን ከአማራው ጠላቶች ጋር አብሮ በግልፅ ጠላትነቱን ያረጋገጠ ስለሆነ በክልሉም ሆነ በፌደራል ያለውን የውክልና ስልጣን ለአማራ ህዝብ በአስቸኳይ እንዲያስረክብ እንጠይቃለን።” የአማራ ግብረሃይል በዩኬ፣ የአማራ ኮሚኒቲ በዩኬ እና ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ግብረሃይል በዩኬ፣ የአማራ ኮሚኒቲ በዩኬ እና ሞረሽ ወገኔ የተሰጠ የአቋም መግለጫ:_ የመንግሥት የመጀመሪያ ሥራው የዜጎችን ደህንነትና ሰላም አረጋግጦ የህይወት ዋስትና ማስጠበቅ ሲሆን ነገር ግን መንግስታዊ ውንብድና እና የዜጎች አፈና፣ ግድያ እየተበራከተ መሄድና በሰላም ወጥቶ መግባት ቅንጦት የሆነባት አገር ላይ መንግሥት አለ ብሎ መዘናጋት ለባሰ የእርስ በእርስ እልቂትና የአገር መፍረስ አደጋን ቆሞ እንደመመልከት ይቆጠራል። አማራ በማንነቱ በጠላትነት ተፈርጆ ዘር የማጥፋት፣ መንግሥታዊ ዘመቻ እንዲቆምና ለሞቱት ፍትህ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው የሞራል ካሣ እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ድጋፍ ተደርጎ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ እና ጋዜጠኞች፣ ወጣቶች ፣ ፋኖዎች በማንነታቸው እና እውነትን በመናገራቸው ብቻ ህግ ተጥሶ በሥቃይ ላይ የሚገኙ የ83 አመቱ አዛውንት አቶ ታዲዮስ ታንቱን ጨምሮ፣ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ እንዲሁም በምስለኔዎች ትዕዛዝ በአማራ ፋኖ ላይ ግድያ፣ እስራት፣ ከበባ እና የተከፈትብን ግልፅ ጦርነት እንዲቆም፣ በለንደን ከተማ እየተካሄደ ያለው ሐምሌ 20 ቀን 2022 የተጀመረው 49ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የቆራጥ እህቶቻችን የርሃብ አድማ የትግሉን አቅጣጫ ፈር ያስያዘና የአማራን ዘር የማጥፋት መንግስታዊ ዘመቻን በመቃወም፣ የአማራዊያን ነፃነት ለማስከበር ቆርጠው በመነሳት በለንደን የተጀመረው የርሃብ አድማ እና ሰላማዊ ሰልፍ በፈረንሳይና በጀርመን ቀጥሏል። ስለዚህ ሁሉም አማራ በያለበት ሆኖ ትግሉን እንዲቀላቀል እንጠይቃለን። 1) የዘመናችን ሂትለር ፣ አብይ አህመድ አሊ ፣ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጥሩነህ ፣ ጄ/ል አበባው ታደሰ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ ደምመላሽ ወ/ሚካኤል ፣ ይልቃል ከፍያለው ፣ ሲሳይ ቶላ ፣ ጌትነት አንለይ ፣ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ ፣አብርሃም አለኸኝ፣ አብርሃም አያሌው ፣ ሰማ ጥሩነህ ፣ ግርማ የሺጥላ አረሮ ወዘተ. በፀጥታ ክፍል ኃላፊዎች እውቅና እና ሙሉ ፈቃድ ፋኖን በማሳደድ አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማዳከም ብሎም ማጥፋት ከአገር በቀል ጠላቶች ጋር ተሰልፈው ወንድሞቻቸውን የሚወጉ ፍርፋሪ ለቃሚ ብአዴኖች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ እንጠይቃለን። 2) አማራ እንደህዝብ በጋራ ከፋኖ ጐን ቆሞ የመጣበትን መንግሥታዊ ጥቃት ለመመከት፣ ለህልውና ዘመቻው ከታጠቁ ፋኖዎች ጋር እንዲቆም እና የልጆቹን ህይወት እንዲታደግ፣ ተላላኪዎችን ህዝቡ አጋልጦ እንዲሰጥ እና መላው አማራ ፋኖ መሆኑን በተግባር እንዲያሳይ እናሳስባለን። 3) የአብይ አህመድ መንግሥት አማራን የማጥፋት ዋና ተግባሩ መሆኑን ከአዲስ አበባ-ቡራዮ፣ ኦሮሚያ እስከ አማራ ክልል ለአራት ዓመት አማራን በጭካኔ አስጨፍጭፎ በተግባር አሳይቶናል። የኦሆዴድ-ኦነግ ሠራዊት በአማራው ላይ ሲፈፅም የነበረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ወደ አማራ ክልል አስፋፍቶ በአሸባሪዎች ትህነግ እና ኦነግ በጋራ ተናበው አማራን በማዋከብ የቀን ቅዠታቸውን ለመፈፀም፣ ፋኖ እና የአማራ ልዩ-ኃይሉን በመግደል፣ በማገት እንዲሁም በተላላኪው ብአዴን እየተፈፀመ ያለው አማራን ትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። 4) ሁሉም አማራ የህልውና ትግሉን በመቀላቀል የድርሻውን እንዲወጣ እና በአንድነት መቆምና በእራሱ በመተማመን ሁለንተናዊ ትኩረቱ ወደ ራሱ ኃይል ብቻ መሆን አለበት ፣ ለአማራ ፋኖነት ታላቁ እሴት እና የልቦናው ውቅር አድርጎ ለዘመናት የኖረ ታላቅ ህዝብ መሆኑን ይገነዘባል። ነገር ግን የዛሬዎቹ የዘመናችን ተላላኪ ብአዴኖች የአማራ እሴት የሆነውን “ፋኖነት” ኢ-መደበኛ ብሎ መፈረጅ ህዝባችንን እንደመናቅ ይቆጠራል። 5) በኦሮምያ ከ200,000 በላይ በመንግሥት በጀት፣ በተሟላ ሎጂስቲክ አሰልጥኖ በሸኔ ስም የተቀመጠው ኃይል፣ አማራን እያረደ እና ንብረት እያወደመ የአማራ ህዝብንና አገራችንን በ60 ዓመት ወደ ኋላ የተመለሰበት ወቅት፣ በብልፅግና-ኦነግ፣ ትህነግ በጥምረት አገርን እያሸበሩ በክህደት፣ ፋኖን፣ ሚሊሻንና ልዩ ሃይላችንን ትጥቅ ለማስፈታት ትላንት በሞጣ፣ በማቻከል፣ በደሴ ፣ በደራ እና በፋኖ ሄዋን ላይ የተፈፀመውን የማይረሳ የብአዴን ክህደት ዛሬም ወገኖቹን ለማስበላት 30 ዲናሩን ተቀብሎ የሦስተኛ ዙር ጦርነቱን እና ፋኖን በማሳደድ ክህደቱን ቀጥሎበታል። የአማራ ህዝብ ሆይ ከአሁኗ ደቂቃ ጀምረህ አይንህን ከፍተህ በንቃት በመጠበቅ ከህልውና ታጋይ ልጆችህ ጎን እንድትቆም እናሳስባለን። 6) ለኦሮሙማ መስፋፋት ሲባል፣ አማራን ከገዛ አገሩ ለማጥፋት አዲሱ ስልትና እንቅስቃሴ፣ በሁሉም አቅጣጫ አማራ ጠል ተላላኪዎችን በማሰማራት ትህነግ እና አማራን ወደ ጦርነት፣ የአማራ እልቂት በኦሮሚያ-ወለጋ ፣ በመተከል፣ በጉራፈርዳ እና በአማራ ክልል ዛሬም የቀጠለው የአማራን ዘር የማጥፋት ጭፍጨፋ እና የሚከፈለው አላስፈላጊ መስዋዕትነት አጥብቀን እያወገዝን፣ለዚህም እየተፈፀመ ያልውን ሰቆቃ የጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግሥት ሙሉ ሃላፊነቱን እንዲወስድ እንጠይቃለን። 7) የአማራ ልጅ ወደ ዩንቨርስቲ ደጃፍ እንዳይደርስ የሚሰራው የተቀነባበረው ደባ ለአለፈው አራት አመት ፈተና ሰርቆ ለተረኞች ከመስጠት እስከ የአማራን ፈተና ውጤት በመቀነስ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ማዕከል እንዳይገባ ሲስተማቲክ ጀኖሳይድ በብርሃኑ ነጋ መሪነት ተፈፃሚ እየሆነ ይገኛል። ይህንም የመጀመሪያ ተጠያቂው የአማራ ተወካይ ነኝ የሚለው ብአዴን በክልሉ ላይ ለሚፈፀመው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ ነው። 8) አማራ ክልል ያሉ ባለሥልጣናት ለጠላት በር በመክፈት፣ ለአማራ ሕዝብ ይቆማሉ የተባሉትን አመራሮች ፣ ፋኖዎችና ወጣቶችን ማሰርና ማሳደድ እንዲቆም የክልሉ ህዝብ ለምን ብሎ እንዲጠይቅና በአራቱም ማዕዘን የመጣበትን ጥላቻና ጠላቱን በተባበረ ኃይል ዛሬም እንደ ትላንቱ የአባቶችህን ታሪክ እንድትደግም፣ ህዝብን ለአደጋ አጋልጠው የፈረጠጡ ተመልሰው ገዳይና አስገዳይ የሆኑት የአማራነት እሴት የሌላቸው ህዝብን ለሽንፈት የዳረጉ አቅመ ቢስ አመራሮች ከስልጣን ወርደው በክህደት ወንጀል እንዲጠየቁ እናሳስባለን። 9) መንግሥት ያወጣውን ህገ መንግሥት ባለማክበር በፍርድ ቤት በነፃ የተለቀቁትን በተረኞች ህገ ወጥ ትዕዛዝ የታፈኑት አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ ስንታዬሁ ቸኮል፣ ተመስገን ደሳለኝ እና እንዲሁም ሌሎች ፋኖዎች ፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች አማራ በመሆናቸው ብቻ በህገወጥ መንገድ የታፈኑ እና የታሰሩ፣ በክልሉና ከክልሉ ውጭ በተለያዩ ስውር ቦታዎች ከ20,000 በላይ ፋኖዎቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። 10) ግርማ የሺጥላ እና መሰል ባንዳዎች ፋኖን የሚያሳድዱ የአማራ ጠላቶች በምንም አይነት ይቅር የማይባል ታሪካዊ ስህተት እየሰሩ እና ቀይ መስመር ማለፋቸውን መላው የአማራ ህዝብ እንዲያውቀው፣ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ዘር የማጥፋት ጭፍጨፋ ለማስቆም ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን የምንሰራበት የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ ስለምንገኝ ሁሉም አማራ እና ሰው የሆነ ሁሉ በአንድነት ትግሉን መቀላቀል ጊዜው የሚጠይቀው የህልውና ዘመቻ ላይ እንገኛለን። ፋኖ ጠላቶቻችን እንደሚሉት ሀገር አፍራሽ እና ጸጥታ አደፍራሽ ሳይሆን ሀገርና ሕዝብ ጠባቂ ስለሆነ መንግስት ፋኖን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን። 11) ብአዴን (የአማራ ብልፅግና) የአማራውን መብትና ህልውና መታደግ የተሳነው ብቻ ሳይሆን ከአማራው ጠላቶች ጋር አብሮ በግልፅ ጠላትነቱን ያረጋገጠ ስለሆነ በክልሉም ሆነ በፌደራል ያለውን የውክልና ስልጣን ለአማራ ህዝብ በአስቸኳይ እንዲያስረክብ እንጠይቃለን። ጠ/ሚ አብይ አህመድ አማራን የማጥፋት እቅድ በተግባር ላይ አውሏል፤ በኦሮሚያ ክልል በስውር በሚያዘው የኦነግ ሠራዊት በአማራው ላይ ሲያደርሰው የነበረውን የዘር ፍጅት ወደ አማራ ክልል አስፋፍቶ፣ ለወረራ እና ለጥቃት ያመቻቸው የአማራ ህዝብ ዳግም በትህነግ ተወሯል። አማራው ከዚህ በኋላ ትጥቅ መፍታት ሳይሆን የተሻለ መሣሪያ መታጠቅ እና ተፈጥሯዊ መብትህን በመጠቀም እራስህንና አካባቢህ ብሎም አገርህን እንድታስከብር እናሳስባለን። በአገራችን ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ፣ ድምፅ አልባው የወለጋ ሆሮጉድሩ ጭፍጨፋ ፣ መሃል አዲስ አበባን ጨምሮ አማራን ማፈናቀል፣ ቤት ንብረቱን መዝረፍ ፣ የእርሻ ውጤቱንና ሰብሉን ማውደም፣ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳያተርፉ መንገድ ዘግቶ በጭካኔ መግደል እንዲሁም በአንድ ጉድጓድ ሰውን እንደቆሻሻ መጣል፣ በጉሙዝ፣ በኦነግ-ብልፅግና እና በትህነግ እየተፈፀመ ያለው ዘር ማጥፋት በአለም አደባባይ የሚወገዝበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም። አንድን መንግሥት መሪ የሚያሰኘው፣ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ሲሆን ብልፅግና ይህን ማድረግ ስላልቻለ በአስቸኳይ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ እንጠይቃለን። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል! https://youtu.be/uw12yE0X_18

Source: Link to the Post

Leave a Reply