ብአዴኖች ከሰማችሁ ምክር እንካችሁ ! ——– ሸንቁጥ አየለ ——-'z የብአዴን ካድሬዎች በአንድ ሳምንት ዉስጥ ጠዋት የተናገሩትን ማታ እየካዱ ህዝባችንን ማወናበዳቸዉን ቀጥለዋል…

ብአዴኖች ከሰማችሁ ምክር እንካችሁ ! ——– ሸንቁጥ አየለ ——-‘z የብአዴን ካድሬዎች በአንድ ሳምንት ዉስጥ ጠዋት የተናገሩትን ማታ እየካዱ ህዝባችንን ማወናበዳቸዉን ቀጥለዋል። መጀመሪያ ጦርነቱ የአማራ ህዝብ ጦርነት አይደለም ሲባሉ “ጦርነቱ የአማራ ህዝብ ጦርነት ነዉ።… ጦርነቱ እርስት የማስመለስ ነዉ” ብለዉ የአማራን ወጣት ቀስቅሰዉ በስሜት ከኦህዴድ/ኦነግ የመከላከያ ሰራዊት በፊት እሳት ላይ ማገዱት። አሁን ደሞ አለቃቸዉ አቢይ ርስት የሚባለዉን ርሱት። ጦርነቱ ህገመንግስት የማስከበር ነዉ ሲላቸዉ አለቃቸዉን ለማስደሰት የስድብ ፕሮፖጋንዳቸዉ. ጭነዉ መጥተዋል። የአሁኑ የስድብ ፕሮፖጋንዳ ደግሞ እራሳቸዉ እርስት እናስመልሃለን ብለዉ ያታለሉትን ወጣት የምናባክ ርስት ነዉ የምትለዉ እያሉ መሳደብን እንደ ስትራቴጂ ይዘዉታል። መጀመሪያዉኑ ጦርነቱ በወያኔ እና በአቢይ ጦር መሃል ነዉ ሲባሉ የለም ጦርነቱ የአማራ ነዉ፡ ርስት የማስመለስ ነዉ ብለዉ ብዙ ለፈፉ። አሁን ደግሞ ሌላ ለፈፋ ይዘዋል። ብአዴኖች ከሰማችሁ ምክር እንካችሁ። አንድ ነገር ዉስጥ ከመግባታችሁ በፊት በደንብ አስባችሁ አንሰላስላችሁ እነመራዋለን የምትሉትን ህዝብ ደህንነት እና ጥቅም አስልታችሁ መራመድን መምከርን እወቁ። ይሄን ብታደርጉ ጠዋት የተናገራችሁትን ማታ ፡ ማታ የተናገራችሁትን ጠዋት እየካዳችሁ በራሳችሁ ደንባራ እስትራቴጂ እየተበሳጫችሁ በካድሬዎቻችሁ በኩል ስለ ህዝብ የሚቆረቆሩትን ሁሉ ከመሳደብ ትቆጠቡ ነበር። አሁንም ጊዜ አላችሁ። በካድሬዎቻችሁ በኩል ያለዉን የስድብ ፕሮፖጋንዳ ርሱት : ቁጭ ብላችሁ ምከሩ። በምክራችሁ ዉስጥ ስለአማራ ያገባናል የሚሉትን እንዲሁም በቅንነት ስለኢትዮጵያ መጻኢ እድል ያገባቼዋል የምትሏቸዉን አካታችሁ ምከሩ። በምክራችሁ አቋራጭ መልስ ላታገኙ ትችላላችሁ። ግን ቢያንስ እንደ ተላላኪ ብቻ አፋችሁን ለስድብ እና ጠዋት ተነግሮ ማታ ለማይደገም ፕሮፖጋንዳ ከማዋል ትቆጠባላችሁ። የአማራን ህዝብ ሰላሳ አመት ሙሉ አዋርዳችሁታል እና ለናንተስ ልምጭ እንጅ ምክር አይገባም ነበር:፡ ግን ምን ይደረግ በአማራ ህዝብ ጫንቃ ላይ ስለተቀመጣችሁ ለሶስት ሽህኛ ጊዜም ቢሆን እየመከርናችሁ ነዉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply