ብዙዎቹ እንደ ጥንብ አንሣ አሞራ አስከሬን እስኪወድቅላቸው የሚጠብቁ ሆነዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ፡፡      ///           አሻራ ሚዲያ    ጥቅምት…

ብዙዎቹ እንደ ጥንብ አንሣ አሞራ አስከሬን እስኪወድቅላቸው የሚጠብቁ ሆነዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት…

ብዙዎቹ እንደ ጥንብ አንሣ አሞራ አስከሬን እስኪወድቅላቸው የሚጠብቁ ሆነዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 09/2013 ዓም ባህር ዳር ///… አገር ከክፉ ቀን የሚታደጋት፣ ችግር ፈቺና ሰብአዊ መብትን የሚያስጠብቅላት ባለሥልጣን፣ ፖለቲከኛ እና ደጋፊ በምትፈልግበት ወቅት ብዙዎቹ እንደ ጥንብ አንሣ አሞራ ለመጥገብና ምቾታቸውን ለማስጠበቅ አስከሬን እስኪወድቅላቸው የሚጠብቁ መሆናቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለፁ። አቶ ኦባንግ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ፖለቲከኛም ሆነ ባለሥልጣን አገሩ ላይ ሲኖር ስለ አገሩ እንደ እናት የሚጨነቅ፤ አገሩ እንዲህ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብታ እያየ የማይታገስ፤ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያመላክት፤ የራሱን ጥቅም ከአገሩ የማያስቀድም መሆን ነበረበት። “አሁን እያየናቸው ያሉ ፖለቲከኛች ሆነ ባለሥልጣን ግን ከዚህ የተለየና ስብዕና የሚባል ነገር የሌላቸው መሆናቸውን በተግባሮቻቸው ዕያሳዩ ነው። ጥቅሙን ብቻ የሚወድና የሚያስቀድም እንደእርሱ አልታየም። እንደውም ብዙዎቹ በሚባል ደረጃ ላይ እንደ ጥንብ አንሣ አሞራ ለመጥገብና ምቾታቸውን ለማስጠበቅ አስከሬን እስኪወድቅላቸው የሚጠብቁ ናቸው “ብለዋል ። መንግሥት ባለሥልጣኑን ሲያስቀምጥ የዜጎች መብትን እንዲያስከብሩ፤ የተሳሳተውን በይቅርታ ማረምና ችግሩን ለመፍታት በአንድነት እንዲራመዱ ነው። ሆኖም ሃላፊነቱ ተዘንግቶ በዝምታ ብዙ ነገሮች እንዲታለፉና ጥቅማቸው እንዲቀጥል እያደረጉ ይገኛል ያሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተጠቃሚነትን ከአገራቸው አስቀድመውም በክፉ ሀሳባቸው ዜጋውን ያባላሉ። ይሄ ደግሞ ዜጎች ስለ ህይወቱ እንዲጨነቁ አድርጓል ብለዋል። ይህም አገርን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እንዳይሠራ መገደቡንም አመልክተዋል። እንደ አቶ ኦባንግ ገለፃ፤ ጥቅም ፈላጊዎቹ ብዙ ነገሮችን በርዘዋል። አብሮነት ሳይሆን ልዩነትን እንዲቀነቀን፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዳይከበር፤ የብሔር ጥላቻና ጎጠኝነት እንዲሰፍን፤ እሴቶቻችን ዋጋ እንዳይኖራቸው፣ ኢትዮጵያ የሚባል ስም እንዳይጠራ አድርገዋል። አገር ጠል ዜጋንም ፈጥረዋል። በተለይም ይህንን ሴራቸውን የተረዳ አካል በየአካባቢው ተሰባስቦ በመደራጀት እውነቱን አውጥቶ ለአንዲት ኢትዮጵያ እድገትና አንድነት መቆም አለበት። ማንም መሞት የለበትም በማለት ቃል ገብቶ መንቀሳቀስ እንዳለበትም አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply