You are currently viewing “ብዙ ወጭ በማውጣት የደከምኩበትን የእቴጌ ጣይቱን ሃውልት ደብረ ታቦር ላይ እንዳላቆም ተከልክያለሁ” ሲሉ ሃውልቱን በባለቤትነት ያሰሩት አቶ ደህናሁን እምሩ ደስታ የተባሉ በጎ ፈቃደኛ ተናገሩ…

“ብዙ ወጭ በማውጣት የደከምኩበትን የእቴጌ ጣይቱን ሃውልት ደብረ ታቦር ላይ እንዳላቆም ተከልክያለሁ” ሲሉ ሃውልቱን በባለቤትነት ያሰሩት አቶ ደህናሁን እምሩ ደስታ የተባሉ በጎ ፈቃደኛ ተናገሩ…

“ብዙ ወጭ በማውጣት የደከምኩበትን የእቴጌ ጣይቱን ሃውልት ደብረ ታቦር ላይ እንዳላቆም ተከልክያለሁ” ሲሉ ሃውልቱን በባለቤትነት ያሰሩት አቶ ደህናሁን እምሩ ደስታ የተባሉ በጎ ፈቃደኛ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አዲስ አበባ ላይ እነ አለም ጸሀይ ወዳጆ በ2012 የእቴጌ ጣይቱ ብጡልን ሃውልት እንዳያሰሩ መከላከላቸው ይታወሳል። ይህ ቁጭት የፈጠረባቸው በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩት አቶ ደህናሁን እምሩ ደስታ በራሳቸው ተነሳሽነትና ወጭ በዛው ዓመት ወደ ደብረ ታቦር በማቅናት ከተለያዩ የከተማው አመራሮች ጋር በመነጋገር የእቴጌ ጣይቱን ሃውልት ያስጀምራሉ። ሃውልቱንም 98% ተጠናቆ የፊታችን የካቲት ወር ለማስመረቅ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ይህ ሁሉ ከተደከመ በኋላ በቅርቡ ተሹመዋል የተባሉት የደብረ ታቦር ከንቲባ አቶ ደሳለኝ በላቸው “የተበላሸን ላስተካከል እንጅ የተበላሸ ላስመርቅ አልመጣሁም” በማለት ሀውልቱን አስመርቀው እንዳያቆሙት ከልክለውኛል ይላሉ። በሀገር ሽማግሌዎች በኩል ለከንቲባው ለማሰረዳት ቢሞከርም አልሆነልኝም፣ ያ ሁሉ ድካሜ መና ቀርቷል ሲሉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። በሁለቱም የቀደሙ ከንቲባዎች ጸድቆ 98% የተጠናቀቀን ሀውልት ከዚህ ማቆም እና ማስመረቅ አይቻልም ተብያለሁ የሚሉት አቶ ደህናሁን ቅሬታቸው መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አድርገዋል። አሁን በጎ ፈቃደኛው አቶ ደህናሁን በሽማግሌ ሞክረው ባለመሳካቱ የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ የደረሰብኝን በደል ይወቅልኝ ብለዋል። አሚማ በእጅ ስልካቸው ደውሎ ያገኛቸው የደብረ ታቦር ከተማ አዲሱ ከንቲባ አቶ ደሳለኝ በላቸው የተነሳውን ቅሬታ ከሰሙ በኋላ “አሁን ስብሰባ ላይ ነኝ፤ አይመቸኝም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply