
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሕዝባቸውን ለማረጋጋት እና ለማጽናናት ወደ ሀገረ ስብከታቸው ለመሄድ ጂማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በኦሮሞ ፖሊሶች ተከለከሉ፤ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ አየር ማረፊያ እንዲቆዩ አድርገዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሕዝባቸውን ለማረጋጋትና ለማጽናናት ወደ ሀገረ ስብከታቸው ለመሄድ ጂማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኦሮሞ ፖሊሶች በመቀበል ኬላ አልፈው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው እንዳይሄዱ ከልክለዋል። ከመከልከልም ባሻገር ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ አየር ማረፊያ እንዲቆዩ አድርገዋል። ብፁዕነታቸው የደቡብ ምዕራበ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ናቸው። በተያያዘም መንግሥት በኦርቶዶክሳውያን ላይ እያደረሰ ያለው እስር እንደቀጠለ ነው ተብሏል። ጥር 29 እና 30/2015 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል:_ 1. ኢ/ር ወንደሰን ተሾመ የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል አባል እና የና/ደ/አሜን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ ሰበካ ጉባኤ፣ 2. ዲ/ን መርከቡ አያሌው የአዳማ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ፣ 3. ወ/ሮ ማኅሌት የአዳማ ማእከል የዜማ መሣሪያ አስተባባሪ፣ 4. ወ/ሪት ወይንሸት ታደሰ የአዳማ ማእከል ሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ጸሐፊ 5. ወ/ሮ ቅድስት በርጋ የአዳማ ማእከል አባል መታሰራቸውን ከማህበረ ቅዱሳን ብሮድ ካስት አገልግሎት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
Source: Link to the Post