ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን ክቡር አቶ አለልኝ አድማሱን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን ክቡር አቶ አለልኝ አድማሱን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን ክቡር አቶ አለልኝ አድማሱን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ገለፀ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን ክቡር አቶ አለልኝ አድማሱን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ገልጧል።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት እስራኤላዊ የሆኑት አዲሱ የእስራኤል አምባሳደር ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ለመቀበል እና ኤምባሲው ከቤተክርስቲያናችን ጋር ሊኖረው ስለሚችለው የሥራ ተግባቦት ለመምከር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መገኘታቸውን አስታውሰው ከ8 ዓመታት በፊት በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ የሚያውቋቸው ቅዱስነታቸውን የታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸውም ቤተ ክርስቲያናችን ከኤምባሲው እና ከእስራኤል መንግሥት ጋር ለምትሰራቸው የጋራ ሥራዎች የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አስረድተው ለሥራቸው መቃናት የቤተ ክርስቲያኒቱ ትብብር እንደማይለያቸው በማረጋገጥ ቡራኬ እንደሰጧቸው ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሓላፊ የድሬዳዋ እና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል ሲል የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት በቴሌግራም ቻናሉ ዘግቧል።
የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጹ እንዳሰፈረው።


173458075 5263289217078989 1338414003405156492 n.jpg? nc cat=111&ccb=1 3& nc sid=8bfeb9& nc ohc=T9uWR6k6CJQAX8smhF5& nc ht=scontent dfw5 1
172571712 5263289383745639 5764319282395943770 n.jpg? nc cat=107&ccb=1 3& nc sid=8bfeb9& nc ohc=z84CunYBPy4AX9yUPCy& nc ht=scontent dfw5 1
Source:- አማራ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply