ብፁዕ ዶክተር አቡነ ገብርኤል ዐረፉ

ብፁዕ ዶክተር አቡነ ገብርኤል ዐረፉ

https://1.gravatar.com/avatar/7f09202441ad3b4b636e88820d6a7061?s=96&d=identicon&r=G
  • የማውቀውን እናገራለኹ” በሚል ርእስ ያዘጋጁት ግለ ታሪካቸው በኅትመት ላይ ነው፤
  • የኤርትራ ኤጲስ ቆጶስ ኾነው ተመድበው ነበር የሐዋርያዊነት አገልግሎትን የጀመሩት፤
  • በነገረ መለኰት የማስተርስና የፒኤችዲ ዲግሪዎች የሞስኮ እና የሐርቫርድ ምሩቅ ነበሩ፤
  • ሥርዓተ ቀብራቸው፣ ነገ እሑድ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

***

የሲዳማ ጌዲዮ እና ቡርጂ ዞኖች አህጉረ ስብከትን በሊቀ ጳጳስነት ያገለገሉት ብፁዕ ዶክተር አቡነ ገብርኤል ዓረፉ፡፡

ብፁዕነታቸው፣ ባለፈው ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ፣ ከእርግና እና ሕመም ጋራ በተያያዘ ከሓላፊነታቸው ተገልለው ረዳት እንዲመድብላቸው መወሰኑ የሚታወስ ሲኾን፣ ዛሬ ቀትር ገደማ በመንበረ ፓትርያርኩ መኖሪያቸው ዓርፈዋል፡፡

የብፁዕነታቸውን የሽኝት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት ለመወሰን፣ ቋሚ ሲኖዶስ ለመሰብሰብ በዝግጅት ላይ ሲኾን፣ ነገ እሑድ፣ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቅዳሴ ውጪ፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተጠቁሟል፡፡

ብፁዕነታቸው፣ ከቤተ ክርስቲያናችን የአብነት ትምህርት ባሻገር፣ ነገረ መለኰትን በዘመናዊ እና ዓይነተኛ መንገድ በከፍተኛ ደረጃ ገብይተዋል፤ ከሞስኮ የማስተርስ እና ከሐርቫርድ ደግሞ የፒኤችዲ ዲግሪዎችን አግኝተዋል፡፡

ትምህርተ ሃይማኖት ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 እንዲሁም ክብረ ቅዱሳን ከተሰኙት መጻሕፍት በተጨማሪ፣ በጋዜጠኞቹ መ/ር ጌታቸው በቀለ እና መ/ር ተስፋዬ ሽብሩ አማካይነት ለረጅም ጊዜ ሲያዘጋጁ የቆዩት ግለ ታሪካቸው፣ “የማውቀውን እናገራለኹ” በሚል ርእስ የኅትመት ሒደቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

በፊት ስማቸው ዶ/ር አባ ኢያሱ ገብሬ ይባሉ የነበረ ሲኾን፤ ጥር 4 ቀን 1972 ዓ.ም. በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ከተሾሙት ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት አንዱ ነበሩ፡፡ በሢመተ ጵጵስናው፣ የኤርትራ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ በመኾን ነበር ሓዋርያዊ አገልግሎታቸውን የጀመሩት፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply