You are currently viewing ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት የዛሬ 86 ዓመት በዛሬው ቀን ነበር፡፡  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ…

ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት የዛሬ 86 ዓመት በዛሬው ቀን ነበር፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት የዛሬ 86 ዓመት በዛሬው ቀን ነበር፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ መስቀልና ወንጌል ብቻ ይዘው የወራሪውን የኢጣሊያ ፋሽስት ነውሩንና ግፉን ፊት ለፊት ታግለው ለሃገራቸውና ለሃይማኖታቸው ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት ሐምሌ 22፣ 1928 ነበር፡፡ አባ ኃይለማርያም ከመጀመሪያዎቹ አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት አንዱ ሆነው ሲመረጡ ስማቸው ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ ሆነ፡፡ በቅኔ፣ በዜማ፣ በመፃህፍት ትርጓሜ የተመረቁት አቡነ ጴጥሮስ በ1921 ዓ.ም ጳጳስነት ከተሾሙ በኋላ የኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን እስከወረረበት ጊዜ ድረስ ሙሉ ወሎንና ከሸዋ መንዝን ሃገረ ስብከታቸው አድርገው ቆይተዋል፡፡ ከዚያ በፊትም በወላይታ በዝዋይ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ በማይጨው ዘመቻ ጊዜ ከንጉሰ ነገስቱ ጋር ሳይለዩ ተዋጊውን ሰራዊት እያበረታቱ አዋግተዋል፡፡ ኢትዮጵያኑ ድል ሆነው ካፈገፈጉ በኋላ በትውልድ አካባቢያቸው በሰላሌ ከተሰማሩት አርበኞች ጋር ተቀላቅለው ቆዩ፡፡ በ1928 ዓ.ም ሐምሌ ወር አዲስ አበባን ከኢጣሊያኖች አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በተደረገው ከበባ በሰሜን በኩል ከዘመቱት አርበኞች ጋር አዲስ አበባ ገቡ፡፡ አርበኞች አልቀናቸውም፤ ድል ሆነው ሲመለሱ ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ ግን ለመመለስ አልፈለጉም፡፡ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ፀሎት አድርሰው በቀጥታ ወደመሐል ከተማ ገብተው ተያዙ፡፡ የኢጣሊያ ሹማምንት አቡነ ጴጥሮስን አባበሉዋቸው፤ የኢጣሊያን ገዥነት ካመኑ በክብር እንደሚያዙ ነገሩዋቸው፡፡ ጳጳሱ ግን እምቢ አሉ፡፡ ገንዘብህ ለጥፋትህ ይሁን ብለው ረገሙ፡፡ እንኳንስ ሰው ምድሩዋ እንዳትገዛለት አወገዙ፡፡ በአቡነ ጴጥሮስ ድርጊት የተናደደው ጀኔራል ግራዚያኒ እንዲገደሉ ወሰነባቸው፡፡ ሐምሌ 22፣ 1928 ዓ.ም ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ በሰንሰለት ታስረው ከአራዳ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንክ በስተምዕራብ ባለው ቦታ ቆሙ፡፡ ከኋላቸው 8 ወታደሮች ጠመንጃቸውን ወድረው ተሰልፈዋል፡፡ በጊዜው በቦታው የነበረው ጋዜጠኛ እንደፃፈው፤ ጥቁሩ ቀሚሳቸው ጭቃ ነክቶታል፤ ወንጌላቸውንና መስቀላቸውን ይዘዋል፡፡ ግድያቸውን እንዲመለከት በትዕዛዝ ወደተሰበሰበው እየተመለከቱ፤ ሕዝቡም ሆነ ምድሩዋ እንዳትገዛላት አወገዙ፡፡ ወዲያው የኪስ ሰዓታቸውን አወጡና አዩ፡፡ ከረፋዱ 5፡30 ሆኖ ነበር፡- ይልና ጋዜጠኛው ስለአሟሟታቸው እንዲህ ይላል፡፡ “አንድ መኮንን ውሳኔውን እየተንቀቀጠ ሲያነብ እሳቸው ግን ያለምንም ስጋት ያዳምጡት ነበር፡፡ ወዲያው ዓይንዎ እንዲሸፈን ይፈልጋሉ? ሲል ጠየቃቸው፡፡ ጳጳሱም “እሱ የናንተ ተግባር ነው” አሉት፡፡ ትዕዛዝ ሲሰጣቸው ወታደሮቹ ተኮሱ፤ በስምንት ጥይትም መቷቸው፡፡ ግን አልሞቱም ነበርና ኮሎኔሉ በሶስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸው ላይ ተኩሶ ገደላቸው፡፡ ሕዝቡም በሀዘን ተሰበረ ይላል፡፡ ጋዜጠኛው ንብረታቸውን ወስጃለሁ ያለው ወታደር እንደነገረው ከሆነ ወንጌላቸውና መስቀላቸው በጥይት ተበሳስቷል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በ53 ዓመታቸው አሁን ሐውልታቸው በቆመበት አካባቢ ተገድለው ባልታወቀ ቦታ ተቀብረዋል፡፡ ከነፃነት በኋላ በ1938 ዓ.ም ለመታሰቢያ እንዲሆን ሐውልት ተቀርፆ ቆመላቸው፡፡ አሁን የሚታየው ሐውልት ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሎ ተቀርፆ የቆመላቸው ነው፡፡ በፍቼም ለሶስተኛ ጊዜ ሐውልት ተቀርፆላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሙሉ ድምፅ በወሰነው መሰረት ሰማዕትነታቸውን አፅድቆ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶላቸዋል፡፡ ሰማዕተ ፅድቅ አቡነ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን የታነፀው የሀገረ ስብከታቸው መቀመጫ በሆነው በፍቼ ነው፡፡ የብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የብዙ የጥበብ ሰዎችን ስሜት እየገዛ ገጣሚዎች ገጥመውላቸዋል፣ ቅኔ አዋቂዎች ቅኔ ዘርፈውላቸዋል፤ ድራማ ተሰርቶላቸዋል፡፡ መረጃው የሸገር ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply