ብ/ጄ ኪዱ አለሙ የተባሉ ግለሰብ ኬንያ ሆነው ለተለያዩ ሀገራት የሀገሪቱን የመከላከያ ሀይሎች ሚስጢርን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር ተገለጸ            አሻራ ሚዲያ…

ብ/ጄ ኪዱ አለሙ የተባሉ ግለሰብ ኬንያ ሆነው ለተለያዩ ሀገራት የሀገሪቱን የመከላከያ ሀይሎች ሚስጢርን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር ተገለጸ አሻራ ሚዲያ…

ብ/ጄ ኪዱ አለሙ የተባሉ ግለሰብ ኬንያ ሆነው ለተለያዩ ሀገራት የሀገሪቱን የመከላከያ ሀይሎች ሚስጢርን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር ተገለጸ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-22/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር ብርጋዴል ጀነራል ኪዱ አለሙ ኬንያ ሆነው ለተለያዩ ሀገራት የመከላከያ ሀይሎች የሀገሪቱን ሚስጢሮች አሳልፈው መስጠታቸውን ፖሊስ አስታውቋል። መርማሪ ፖሊስ ይህንን የገለጸው ተጠርጣሪው ዛሬ ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው 13 ቀን ውስጥ በርካታ የምርመራ ስራ መስራቱን አብራርቷል። እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ኬንያ ሆነው ለተለያዩ ሀገራት የመከላከያ ሀይሎች የሀገሪቱን ሚስጢሮች አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበርና ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሲፈጸም ለጸረ ሰላም ሀይሉ በሳተላይት በመጠቀም ወታደራዊ አመራርነትና ድጋፍ ሲሰጡ እንደነበር ተገልጿል። በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትን የሚያመላክቱ የጉዳት መጠን ማስረጃዎችን ማምጣቱንም ለችሎቱ አስረድቷል። የምርመራ መዝገቡንም በሰውና በሰነድ ማስረጃ አጠናክሮ ለሚመለከተው አካል ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ጠቁሟል። ተጠርጣሪ ከጠበቃቸው ጋር ተወክለው የተገኙ ሲሆን÷ በኬኒያ አንድ ዓመት ከስምንት ወር በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት አንድም ቀን ከኤምባሲው ወጥተው እንደማያውቁ አስረድተዋል ነው የተባለው። በመርማሪ ፖሊስ የቀረበው የተጨማሪ ጌዜ መጠየቂያ ምክንያቶች ተገቢ አይደሉም ሲሉ ተከሳሹ ተከራክረዋል። የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ለቀሪ ምርመራ ማከናወኛ 11 ተጨማሪ ቀናት ለፖሊስ ፈቅዷል። ውጤቱን ለማዎቅ ለጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በቀጠሮ ቀንም መዝገቡ እንዲቀርብ ማዘዙ ነው የተገለጸው። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply